Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትኦራንጉታን

ኦራንጉታን

ቀን:

ኦራንጉታን (Orangutan) በእስያ ብቻ የሚገኝ ኤፕ (Ape) ነው፡፡ ኦራንጉታኖች ለአቅመ ርቢ የሚደርሱበት ዕድሜ ስምንት ሲሆን፣ የእርግዝናቸው ርዝማኔ ከስምንት እስከ ዘጠኝ ወር ይሆናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ በዛፍ ላይ የሚኖሩ ኤፖች ናቸው፡፡ በዚህም ትልቁ የዛፍ ላይ አጥቢ እንስሳ በመባል ይታወቃሉ፡፡ ልጆቻቸውም ለረዥም ጊዜ (እስከ ስድስት ዓመት) ከወላጆቻቸው ተጠግተው ያድጋሉ፡፡ አንድ ልጅ የሚወልዱት በየስምንት ዓመት ርቀት ነው፡፡ ይህም ከአጥቢዎች ሁሉ የራቀ ነው፡፡ ወንዱ የጉሮሮውን ከረጢት ልዩ ድምፅ ለማውጣት ይጠቀምበታል፡፡ ይህም በጫካው ውስጥ የገደል ማሚቶ በመፍጠር ሴቶቻቸውን ለመጥራትና ያሉበትን ለማስተዋወቅ ሲረዳ፣ ሌሎች ወንዶችን ደግሞ ያባርራል፡፡ እጆቻቸው እንደሰው ሲሆኑ አራት እረዣዥም ጣቶችና አንድ መዳፍ ማቋረጥ የሚችል አውራ ጣት (እንደ ሰው) አላቸው፡፡ የአስተሳሰብ ደረጃቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ዝናብ በሚሆንበት ጊዜ ቅጠልን እንደ ዣንጥላ የመጠቀም ችሎታ አላቸው፡፡ ይህንኑ ቅጠልም እንደ ሲኒ አድርገው ውኃ ለመጠጣት ይጠቀሙበታል፡፡

በየቀኑ ማታ ማታ ጎጆ ከቅጠልና ከዛፍ ግንጣይ ሠርተው በውስጡ እጥፍጥፍ ብለው ይተኛሉ፡፡ መዋኘት አይችሉም፡፡ እጃቸው በጣም ረዥም በመሆኑ ቁርጭምጭሚታቸው ጋ ይደርሳል፡፡ ወንዱ እጁን ሁለት ሜትር ያህል ስፋት ይዘረጋል፡፡ ግለኛ ስለሆኑ ወንድና ሴትም ለርቢ ከተገናኙ በኋላ ወዲያው ይለያያሉ፡፡ በዚህም ከቅርብ ዘመዶቻቸው ቺምፓዚና ጎሬላ ይለያሉ፡፡ ወንዱ በሚያረጅበት ጊዜ ፊቱ ድርብርብ ጉንጭ ሲያወጣ ጉሮሮው ደግሞ ከረጢት ይፈጥራል፡፡ 97 በመቶ ያህል ከሰው ልጅ ጋር  ተመሳሳይነት ሲኖራቸው ስሜታቸውን በተለያየ መልኩ ይገልጻሉ፡፡ ለምሳሌ ሲናደዱ የዛፍ ቅርንጫፍ በመወዝወዝና ለምቦጫቸውን በመጠብጠብ ስሜታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ራሳቸውን ለማስተዋወቅ ደግሞ ረዥም ጩኸት ያሰማሉ፡፡

  • ማንይንገረው ሽንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...