Sunday, April 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትየድመት ጢም

የድመት ጢም

ቀን:

ድመቶች አብዛኛውን ጊዜ በጨለማ ንቁ ናቸው። ከጨለመ በኋላ በአቅራቢያቸው ያሉ ነገሮችን ለይተው ለማወቅና አድነው የሚበሉትን እንስሳ ለመያዝ የሚረዷቸው ጢሞቻቸው እንደሆኑ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል የሚለው ጄደብሊው ዶትኦርግ ነው

የድመት ጢሞች የሚበቅሉት ብዙ የነርቭ ጫፎች ባሏቸው ሕብረ ሕዋሳት ላይ ነው። እነዚህ ነርቮች በአየሩ ላይ የሚፈጠረው በጣም ትንሽ እንቅስቃሴ እንኳ ይሰማቸዋል። በዚህም የተነሳ ድመቶች በአቅራቢያቸው ያሉ ነገሮችን ባያዩአቸውም እንኳ መኖራቸውን ማወቅ ይችላሉ፤ ይህ ደግሞ በጨለማ እንደሚጠቅማቸው ግልጽ ነው።

የድመት ጢሞች ትንሹም እንቅስቃሴ ቶሎ የሚሰማቸው መሆኑ አንድ ነገር ወይም አድነው የሚበሉት አንድ እንስሳ ያለበትን ቦታና የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለይተው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም ድመቶች በአንድ ክፍተት በኩል ለማለፍ ሲሞክሩ ጢሞቻቸው የክፍተቱን ስፋት ለመለካት ይረዷቸዋል።

ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደገለጸው ከሆነ፣ የድመት ጢም ያለውን ጥቅም በተመለከተ ማወቅ የተቻለው ከፊሉን ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ድመቱ ጢሙ ከተቆረጠበት ለጊዜውም ቢሆን እክል እንደሚገጥመው ታውቋል።

የሳይንስ ሊቃውንት፣ የድመት ጢሞችን ንድፍ በመኮረጅ በእንቅፋቶች መሃል እየተሹለከለኩ ለመሄድ የሚያስችሉ ጠቋሚ መሣሪያዎች ያሏቸው ሮቦቶች ለመሥራት ጥረት እያደረጉ ነው። ኢዊስከርስ ተብለው የተጠሩት እነዚህ ጠቋሚ መሣሪያዎች ‹‹ለተራቀቀ የሮቦት ቴክኖሎጂ፣ የተለያዩ መሣሪያዎችን ለአጠቃቀም ምቹ ለማድረግ እንዲሁም በባዮሎጂ መስክ የተለያየ አገልግሎት›› እንደሚኖራቸው በካሊፎርኒያ የሚገኘው የበርክሊ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሊቅ የሆኑት አሊ ጃቪ ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኦቲዝምን ለመቋቋም በጥምረት የቆሙት ማዕከላት

ከኦቲዝም ጋር የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ...

አወዛጋቢው የወልቃይት ጉዳይ

የአማራና ትግራይ ክልሎችን እያወዛገበ ያለው የወልቃይት ጉዳይ ዳግም እየተነሳ...

ተጠባቂው የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የውድድር መለኪያ የሆነው የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በኢትዮጵያ

የሞባይል ገንዘብ ዝውውር የሞባይል ስልክን በመጠቀም ሊገኙ የሚችሉ የፋይናንስ...

የአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ

በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት...