Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሚስቱን በመግደል የተጠረጠረ ግለሰብ እጁን ለፖሊስ ሰጠ

ሚስቱን በመግደል የተጠረጠረ ግለሰብ እጁን ለፖሊስ ሰጠ

ቀን:

– ከተጋቡ ገና ሁለት ወራቸው ነበር

–  ተጠርጣሪው ከስድስተኛ ፎቅ ተከስክሶ ተርፏል

ሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ድል ባለ ሠርግ ያገባትን ሚስቱን ሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. አንቆና ደብድቦ ገድሏል የተባለው ተጠርጣሪ፣ እጁን ለፖሊስ መስጠቱ ታወቀ፡፡

ተጠርጣሪውና ሟች ወ/ሮ በእምነት ገረመው ሰኔ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. እስከ ሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ድረስ ሲዝናኑ አምሽተው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ስሙ የረር በር አካባቢ ወደ ተከራዩበት ቤት ያመራሉ፡፡ በዕለቱ በተፈጠረ ጊዜያዊ ግጭት ተጠርጣሪ አንገቷን ይዞ በቦክስ ሲመታት ሟች ከወደቀችበት ልትነሳ ባለመቻሏ፣ ተጠርጣሪው ተጠግቶ ትንፋሽ እንዳላትና እንደሌላት ሲያዳምጥ ሕይወቷ ማለፉን በማረጋገጡ ቆልፎባት መሰወሩን የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ተጠርጣሪው ለጊዜው የት እንዳለ ባይታወቅም ወዳከራዩዋቸው ሰዎች በመደወልና ድምፁን የሌላ ሰው ድምፅ በማስመሰል፣ የራሱን ስምና የሟችን ስም በመጥራት እንዲያቀርቡለት ይጠቅይ እንደነበር ምንጮች ተናግረዋል፡፡

አከራዮቹ እንደሌሉና በራቸውም ዝግ እንደሆነ ሲነግሩት ስልኩን ዘግቶ በድጋሚ በመደወል እንዳገኛቸው በመግለጽ አመስግኖ መዝጋቱንም አክለዋል፡፡ የሟች አክስሬን እየሸተተና በተቆለፈው በራፍ አካባቢ ዝንቦች በመብዛታቸው አከራዮች ተጠራጥረው ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቃቸው፣ ፖሊስ ደርሶ በሩ ሲከፈት ወ/ሮ በእምነት ሕይወቷ አልፎ መገኘቷንም ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ለአራት ቀናት ያህል ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ሲጋባ የቆየው ተጠርጣሪ ሰኔ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰሜን ሆቴል ስድስተኛ ፎቅ ላይ በመውጣት ራሱን ወርውሮ ለመግደል ቢጥርም፣ ያረፈው መሬት ላይ ሳይሆን በሌላ ቤት ጣሪያ ላይ በመሆኑ ሊተርፍ እንደቻለ ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡ ተጠርጣሪው እጁ ላይ ጉዳት በመድረሱ ወደ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ተወስዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ እህቱ ቤት የሄደ ቢሆንም፣ ከእህቱ ቤት በማግሥቱ መጥፋቱ ተጠቁሟል፡፡ ነገር ግን ሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት  በምርመራ ላይ መሆኑም ታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ