Thursday, June 8, 2023

የሰላም ማስከበር ፍልስፍና አዳዲስ ፍላጎቶች

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች መካከል ሰላም የመጠበቅና የማስከበር ሥራ ዋነኛው ነው፡፡ ‹‹የአንድ አገር ሰላምና ፀጥታ መደፍረስ የሁሉም አባል አገሮች ሰላም መደፍረስ ነው፤›› የሚል የጋራ ደኅንነት ፍልስፍናን መመርያው ያደረገው ተመድ በአባል አገሮች መካከል፣ አልያም በአንድ አገር ውስጥ ግጭት ሲከሰት ሰላም አስከባሪ ኃይል ማሰማራት የድርጅቱ ዋነኛ ሥራ ነው፡፡

ተመድ እ.ኤ.አ በ1945 ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ካሰማራቸው ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት የተሰማሩት አፍሪካ ውስጥ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአፍሪካ ደረጃ ከተከናወኑት ሰላም የማስከበር ተልዕኮዎች የኢትዮጵያ ተሳትፎ ቀዳሚነት ይይዛል፡፡ በላይቤሪያ፣ በሩዋንዳና በመሳሰሉት አገሮች የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች አኩሪ ተግባር መፈጸማቸው ይወሳል፡፡ በዚህም አገሪቱ ከፍተኛ ዕውቅና አግኝታበታለች፡፡

የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል በአፍሪካ አገሮች የሚያከናውናቸውን ተግባራት  ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመተባበር የሚያከናውን ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ ለኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ አገሮች ማለትም በሱዳን፣ አሁን ደግሞ በደቡብ ሱዳን እንዲሁም በሶማሊያ (አሚሶም) ያሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር በድንበር ውዝግብ ምክንያት ግጭት ውስጥ በገባችበት ወቅትም አንሚ (UNMEE) በመባል የሚታወቀው የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል፣ በሁለቱም አገሮች ድንበር አካባቢ ረዘም ላለ ጊዜ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ሰላም የማስከበር ተልዕኮ በራሱ መፍትሔ ባይሆንም የተጋጋለ ግጭት በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ በሁለት ተፋላሚ ወገኖች የሚደረግ ተኩስ እንዲቆም ጊዜያዊ መፍትሔ ይሰጣል፡፡ ይህ ሰላም የማስከበር መሠረታዊ ፍልስፍና ባይለወጥም፣ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዎች አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለዋወጡ መምጣት እንዳለባቸው የሚጠቁሙ ጥናቶች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡

የካቲት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጎልደን ቱሊፕ ሆቴል ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ የሆኑ ዲፕሎማቶችና የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች በተገኙበት ይፋ የሆነው ጥናታዊ መጽሐፍ “UN Peacekeeping Doctrine in a New Era Adapting to Stabilization, Protection and New Threats” በሰላም ማስከበር መርሆዎች ላይ አዳዲስ የመከራከሪያ ነጥቦችን ይዳስሳል፡፡

በሦስት አጥኚዎች ተዘጋጅቶ የቀረበው ይኼው ጥናት የተመድ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዎች ዓላማ የሚያሰፋና ስኬታማነቱን ከፍ ያደርጋል በሚል በበርካታ ታዳሚዎች ሙገሳ የተቸረው ሲሆን፣ ሁለቱ አጥኚዎች በኖርዌይ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም የሚሠሩ ናቸው፡፡ ሦስተኛው አጥኚ ደግሞ በቶክዮ ዩኒቨርሲቱ (ጃፓን) ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ በመጽሐፉ ላይ በመመርኮዝ የሚመለከታቸው አካላት ሐሳባቸው እንዲያካፍሉ ተደርጎ መጠነኛ ውይይትም ተካሄዷል፡፡

የምክክር፣ የጥናትና የትብብር ማዕከል ‹‹ትሬይኒንግ ፎር ፒስ›› ከሚባል የኖርዌይ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነበር መድረኩ የተዘጋጀው፡፡

ለውይይቱ መነሻ ይሆን ዘንድ ከመጽሐፉ አዘጋጆች መካከል ጆን ካርልስሩድ፣ እንዲሁም ሴድሪዲ ኮኒንግ የተባሉት ተመራማሪዎች በተመረጡ የመጽሐፉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በአዲሱ ዘመን ማለትም አዲስ የኃይል አሠላለፍ እየተስተዋለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የሰላም ተልዕኮዎች አዳዲስና ተጨማሪ ዓላማዎች ለማካተት ራሳቸው ከሁኔታዎች ጋር መጣጣም እንዳለባቸው በመጠቆም የጥናቱ አንኳር ጉዳዮችን አቅርበዋል፡፡

የጋራ ፍልስፍና የመፍጠር አስፈላጊነት በዋናነት ጥናቱ በቅድመ ሁኔታነት የሚያስቀምጥ ሲሆን፣ የሚታወቁት ዘልማዳዊ የተመድ የሰላም ማስከበር መርሆዎችን ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ማጣጣም ካልተቻለ ስኬታቸው ጥያቄ ውስጥ የሚገባ እንደሆነ ይተነትናል፡፡ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ በተለይ በአምስቱ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት መካከል ያለው የፍልስፍና ልዩነት፣ እንዲሁም ሰላም አስከባሪ ኃይል በማዋጣት ቀዳሚ በሆኑት  አገሮች መካከል ያለው የአስተሳሰብና ፍላጎት ልዩነት ላይ የተመረኮዘ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ሰላም የማስከበር ተልዕኮዎች የቆዩ አስተሳሰቦች በተጨባጭ መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የፈጠሩት ክፍተትና ግጭት በመጽሐፉ ተዳሷል፡፡

ከዚህ በፊት ተመድ ተቋማዊ ማሻሻያ እንዲያደርግ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች ጥያቄ የሚያነሱበት ሲሆን፣ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ፍልስፍናውም ከዚሁ አንፃር እንደ አዲስ እንዲቃኝ አጥኚዎቹ ያሳስባሉ፡፡

በመጽሐፉ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል የቀድሞ የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊና የሰላም ማስከበር ዲፓርትመንት ኃላፊ በአሁኑ ወቅት የክራይሲስ ግሩፕ (ICG) ኃላፊ ሆኑት ጂን-ማሪ ጉሄኖ ይገኙበታል፡፡ እሳቸው እንደሚከራከሩት በሥራ ላይ ያለው የሰላም ማስከበር ፍልስፍና አሁን እየተከሰቱ ያሉትን ግጭቶች ለመፍታት ፋይዳው የወረደ ነው፡፡

በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይል ዋና ኮማንደር በመሆን ያገለገሉት ሌተና ጄኔራል ካርሎስ አልቤርቶ የተባሉ ባለሙያ ደግሞ፣ ከኒውዮርክ እስከ ሰላም የሚከበርበት መስክ የሚገኙ ሰላም በማስከበር የተሰማሩ ሰዎች ማንበብ ያለባቸው መጽሐፍ ነው በማለት የራሳቸውን ግምገማ አቅርበዋል፡፡

መጽሐፉን መሠረት አድርጎ የተደረገውን ውይይት ተመድ የአፍሪካ ልዩ ተወካይ አድርጎ የሾማቸው አምባሳደር ኃይሌ መንቆርዮስ በሊቀመንበርነት የመሩት ሲሆን፣ በአፍሪካ ኅብረት የፖሊሲ ጥናት ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ጂዴ ማርቲንስ በተለይ በአፍሪካ ስላለው ሰላም የማስከበር እንቅስቃሴ አስመልክተው ንግግር አድርገዋል፡፡

አምባሳደር ኃይሌ መንቆርዮስ የወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን መርህና መሰል ጉዳዮች አስመልክተው ማሊን በምሳሌነት በመጥቀስ፣ የተመድ ፀጥታ ምክር ቤት ራሱን ከቀደሙ መርሆች ምን ያህል እየራቀ መምጣቱን ማሊ አመላካች እንደሆነች አስረድተዋል፡፡

 ዶ/ር ጂዴ በበኩላቸው ማሊን፣ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን (ዳርፉር) ያለውን ሰላም የማስከበር እንቅስቃሴ መሠረት አድርገው አንዳንድ ምልከታዎች አቅርበዋል፡፡ ገለልተኝነት፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና ዘለቄታዊ ግጭት አፈታትን መሠረት አድርጎ የፀጥታው ምክር ቤት ከመከላከል ወደ ማረጋጋትና አጥፊን የማጥቃት ፍልስፍና መከተል መቀየር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ኅብረትን ከመሳሰሉ አኅጉራዊ ድርጅቶች ጋር በጋራ ሊሠራበት የሚችል ተቋማዊ አሠራር እንዲፈጠርም ጠይቀዋል፡፡

ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል አንዱ በሰላም ማስከበር ሥራ ተሰማርተው ለረዥም ጊዜ የቆዩ ባለሙያ፣ በኮንጎ ከ60 ዓመታት በፊት ጀምሮ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ የነበረ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ምንም ለውጥ አለማምጣቱን ጠቅሰው፣ ሌላ ሰላም የማስከበር ፍልስፍና እንዲቀረፅ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር በበኩላቸው፣ በዳርፉርና በደቡብ ሱዳን ያለው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ መሠረት አድርገው አስተያየት ሲሰጡ፣ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ የንፁኃን ዜጎችን ሕይወት መታደግ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ራሳቸውን በመጠበቅ ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረዋል፡፡

ሌላ አስተያየት ሰጪ ዲፕሎማት በበኩላቸው፣ በተለይ የሶማሊያ ጉዳይን ለአብነት አንስተው የሰላም ማስከበር ዓላማው የአገሪቱን የፀጥታ ኃይል ማጠናከር፣ የፀጥታ ተቋማት እንዲጎለብቱና በዘላቂነት ችግሮችን ለመፍታት እንዲረዳ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

አምባሳደር ኃይሌ በማጠቃለያ ሐሳባቸው፣ ‹‹ጉዳዩ ቀላል አይደለም፡፡ ሰፋ ያለ ክርክርና ውይይት ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ተመድ የበለጠ ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲሆን ከሚቀርበው ተደጋጋሚ ጥያቄ በተጓዳኝ የሚታይ ጉዳይ ነው፤›› ብለዋል፡፡

R1759 politics

Tigist

የሰላም ማስከበር ፍልስፍና አዳዲስ ፍላጎቶች

በየማነ ናግሽ

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -