Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ሕዝብ ዙርያ አገር አቀፍ ጉባኤ ያካሂዳል

  የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ሕዝብ ዙርያ አገር አቀፍ ጉባኤ ያካሂዳል

  ቀን:

  የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ሕዝብ ጥናት ትምህር ክፍል በሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎሜሽን ዘመን መባቻ ትኩረት ያሻዋል ባለው የሥነ ሕዝብና ልማት ጉዳይ ላይ አገር አቀፍ ጉባኤ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡ የትምህርት ክፍሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ክንፈ ገብረ እግዚአብሔር ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የጉባኤው ዓላማ በየዓመቱ ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር እንዴት ከመንግሥት የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች አፈጻጸም ጋር ማጣጣም ይቻላል የሚለውን ምክረ ሐሳብ ለማመንጨት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

  ብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ጉባኤውን በማሰናዳት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተባባሪነት እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ክንፈ፣ ዩኒሴፍና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም  በጉባኤው ዝግጅት ላይ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ገልጸዋል፡፡ ከሐምሌ 24 እስከ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰማዕታት አዳራሽ በሚካሄደውና   ከ50 በላይ ጥናታዊ ጽሑፎች በሚቀርቡበት የሥነ ሕዝብ ጥናት ተመራማሪዎችና የፖሊሲ አርቃቂዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

  ለሦስት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ ላይ በሥነ ሕዝብ ዙሪያ ለሚሠሩ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ሥልጠና እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡

  በሥነ ሕዝብና ልማት ላይ ከዚህ በፊት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የተካሄደ ሲሆን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የሚካሄደው ይኸው አገር አቀፍ ጉባኤ ሦስተኛው እንደሚሆን ታውቋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img