Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

እኔንና መሰሎቼን ሰሞኑን የሚያነጋግሩን በርካታ ጉዳዮች በዚህ ዓምድ በጣም ቢበዙበትም፣ አስገራሚ በሆኑ ዋና ዋና ክስተቶች ላይ በመንተራስ እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡፡ እስቲ ይኼንን ገጠመኝ ከአሜሪካ አካባቢ ከሚወሩ ጉዳዮች ልጀምርላችሁ፡፡ እንግዲህ ሁላችሁም እንደሰማችሁት በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ሲልቨር ስፕሪንግ/ቨርጂንያ የተለመደው የዳያስፖራ እግር ኳስ ውድድር ሲካሄድ ነበር፡፡ ለዚህ ውድድር ከተለያዩ ስቴቶች በርካታ ወገኖቻችን አካባቢውን አጨናንቀውት ነበር፡፡ ማጨናነቅ ብቻ ሳይሆን ደመቅመቅ ብሎ ሰንብቷል፡፡

አንድ ወዳጄ እንደነገረኝ ግን ሐባሻ ምን ነክቶታል እስኪባል ድረስ የአንዳንዶቹ ባህሪ አስደንጋጭ ነበር፡፡ ድሮ እዚህ አገር አንድ ሰው በስንት ዓመቱ ሲመጣ እንደ ንጉሥ ይታይ ነበር፡፡ ዕድሜ ለጊዜ አሁን ዳያስፖራ ይሁን አገር በቀል ማንም ዞር ብሎ አያየውም፡፡ የአገሬ ሰው ድህነት አንዳንዴ ሸብረክ ቢያደርገውም፣ የቅኝ ተገዥነት መንፈስ ስለሌለበት ማንም መጣ ማን ግድ የለውም፡፡ ሁሉንም እንዳመጣጡ አስተናግዶ ይሽኛል፡፡ አሜሪካ ውስጥ ግን ያውም በዚህ ዘመን የመናናቁ ነገር ይገርም ነበር አሉ፡፡

አንዱ ወዳጃችን በፌስቡክ ገጹ ላይ፣ ‹‹የአገር ልጅ እንዲህ በርከት ብሎ ሲታይ እንዴት ደስ ይላል መንገዱን፣ ቤቱን፣ አገሩን፣ ሞቅ ደመቅ ፈካ ማድረጋችሁ ተመችቶናል፡፡ ኧረ እንዲያውም ሁሌ ኑልን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንዶቻችሁ፣ እናንተ ከአሜሪካ የመጣችሁ እኛ ደግሞ እንዲያውም ጭራሽ ከጨለንቆም ያልወጣን ይመስል የምታሳዩን አንጀባ በጣም ያስተዛዝባል፡፡ ምናለበት ስንተዋወቅ ባንናናቅ? የአገር ቤት ሰው ዳያስፖራ አያሳየኝ ያለው አናንተን እያየ ነው ለካ? እስኪ በኳስ ምድር አንጀባውን ረጋ…›› ብሎ ነበር፡፡

- Advertisement -

ይህ ወዳጃችን በተለይ ‹አንዱን› በማለት እነዚህ ወገኖች ጋብ እንዲያደርጉ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ‹‹በአካባቢው በርካታ የሐበሻ ቤቶች ስትዝናኑ አስተናጋጆቹ እህቶቻችንን በተቻለ ጨዋነትና ርህራሔ ተግባቡዋቸው፡፡ እንኳን የእናንተ ዓመታዊ ‹ስፔሻል› ገሪባነት ተጨምሮ፣ የእኛንም ቋሚ ገሪባነት የሚቋቋሙት በመከራ ነው፡፡ የፈለገ ቲፕ ብታደርጉ ሰብዓዊነታቸውን የመግፈፍ መብት የላችሁም፡፡ ጨዋነት ‘Is the best form of’ አራዳነት፤›› ብሎ ሰዎቹ ዲሲ ውስጥ ኳስ አይተውና ቢራ ጠጥተው ብቻ እንዳይሄዱ፣ ይልቁንም ለዕድሜ ልክ የሚሆን ዕውቀት እንዲያካብቱ የከተማዋን ምርጥ ሙዚየሞች እንዲጎበኙ አሳስቧል፡፡ እግዚአብሔር ይስጠው፡፡ እንግዲህ እንዲህ ያለ ደስ የማይል ነገር ከአሜሪካ ስትሰሙ ይከፋችኋል አይደል? አዎ በጣም ደስ አይልም፡፡

እንዲህ እያልን እንቀጥል፡፡ በወዲያኛው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ ዋይት ሐውስ በራፍ የፕሬዚዳንት ኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት ለመቃወም የወጡ ሰዎች ነበሩ፡፡ በሥፍራው የሚገኘው የቪኦኤ ጋዜጠኛም ሥራውን በማከናወን ላይ ነበር፡፡ በዚህ መሀል ድንተኛ የሆነ ክስተት ያጋጥማል፡፡ ድራማ ለማለት ከባድ ነው፡፡ ለተቃውሞ የመጡት የዳያስፖራ ወገኖቻችን ሔኖክ ስማእግዜር የተባለ የቪኦኤ ጋዜጠኛን መጎሸምና መሳደብ ይጀምራሉ፡፡ ሰዎቹ የኦባማን ጉብኝት ለመቃወም የመጡት የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን በማሰር ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ያፍናል በሚል ሰብብ ነው፡፡ እነሱ ጋዜጠኛውን መቃወም መብታቸው ቢሆንም፣ የሚቃወሙት መንግሥት ይፈጽመዋል የሚሉትን ተግባር ሲፈጽሙ ምን ይባላል? ስህተትን በስህተት ለማረም የሚነሱ እንዲህ ዓይነቶቹስ ምን ይባላሉ? ሌላው ወዳጃችን ይኼንንም ጉዳይ በሚመለከት በሰጠው አስተያየት ብዙዎቹ ድንፈኛ ግለሰቦች አውግዘውታል፡፡ ሰድበውታል፡፡ ምራቃቸውን የዋጡት ግን ድርጊቱን በማውገዝ ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡

‹‹መቼም ያገራችን ሰው እጅግ አምሮበታል፤›› ያለው ይኼው ወዳጃችን፣ ‹‹…በዲሲ ሠልፍ ላይ የቪኦኤው ጋዜጠኛ ሔኖክ ሰማእግዜር ትዕይንቱን ለመዘገብ ሄዶ የደረሰበትን አሳፋሪ ተግባር ተመለከትን፡፡ እነርሱን በግልጽና መሉ በመሉ የማይደግፍ ጋዜጠኛና ግለሰብ በዓይናቸው የማይፈልጉ ሰዎች፣ ኦባማን የሚቃወሙት ለዴሞክራሲ አስበው ነው ማለት ቀልድ ይሆናል፡፡ እነዚህ ሰዎች ለሠልፉ የመጣውን ሰው ሁሉ እንደማይወክሉ አውቃለሁ፡፡…ያዳላል ለማለት ጋዜጠኛ ቃለ መጠየቅ አልሰጥም፣ መረጃ አላካፍልም ማለት ያባት ነው ከጠቀመ፡፡ መሳደብ፣ ማዋከብና መጎሸም ግን ሊነወር የሚገባው ክፉ ልማድ ነው፡፡ …አጠገቡ ያለውን ጋዜጠኛ ሔኖክ የሚሰድብና የሚጎሽም ሠልፈኛ ‹እስክንደር ይፈታ፣ ርዕዮት ትለቅቅ› ቢል ቀድመው የሚታዘቡት እስክንድርና ዕርዮት ናቸው…አለበለዚያማ ኢሕአዴግ ሌላ ምን አደረገ? ለእርሱ የማይጥሙትን ጋዜጠኞች ሰሰብ እየፈለገ ከማሰርና ከማሳደድ ውጪ…›› ነበር ያለው፡፡ ጽንፈኛነትን ከጨለማ እንዴት እንለየው ታዲያ? ይኼ ችግር የዳያስፖራው ብቻ ሳይሆን እዚህ ያሉ አንዳንድ ወገኖቻችን ችግር መሆኑ ይሰመርበት፡፡

እና ወዳጆቼ ለንግግር ነፃነት፣ ለሰብዓዊና ለዴሞክራሲያዊ መብቶች እንታገላለን የሚሉ ወገኖቻችን ራሳቸው አፋኝ መሆናቸውን ሲያሳዩን ምን ይባላል? ወገኑን የሚንቅ፣ የሚያዋርድ፣ የሚያጎሳቁልና ሰብዓዊ ክብሩን የሚነካ ግለሰብ ወይም ቡድን እስከ መቼ እያፏጨብን ይኖራል? ይህች የተከበረች አገር እጅግ በጣም በርካታ ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ያፈራች ናት፡፡ ከዚህች የተከበረች አገር ማህፀን የወጡ ሰዎች አጥፍተው ሲገሰፁ አይሰሙም፡፡ ይሳደባሉ፡፡ ሰብዕናን ያዋርዳሉ፡፡ ማንነትን ያንኳስሳሉ፡፡ እነዚህ ናቸው ስለመብት የሚናገሩት? እነዚህ ናቸው ለሰው ልጅ ክብር የሚታገሉት? እኔ ስለነዚህ አፍራለሁ፡፡

      በአንድ ወቅት አሜሪካ ሂጄ ነበር፡፡ የተለያዩ ግዛቶችን ተዘዋውሬ (በሥራ ጉብኝት) ካጠናቀቅኩ በኋላ ለ15 ቀናት ዲሲ ከርሜ ነበር፡፡ የመጀመርያ ትዝብቴ በርካታ ወገኖቼ መሠረታዊ የሆነ ችግር እንዳለባቸው መረዳቴ ነበር፡፡ እጅግ በጣም ጥቂቶች በትልቁ ድምፃቸው የሚሰማ ስለሆነ ብዙኃኑን ፀጥ አሰኝተውታል፡፡ የደርግና የኢሕአፓ ዘመንን አስታወሰኝ፡፡ ስለጽንፈኛ ፖለቲከኞቹ በየቤቱ ካልሆነ በስተቀር በአደባባይ አይወራም፡፡ ወይ አሜሪካና ዴሞክራሲያዋ ያሰኛል፡፡ በተለይ ለኢትዮጵያውያን፡፡ ሌላው ችግር አብዛኞቹ የአሜሪካን ሚዲያ አይከታተሉም፡፡ በቋንቋ ችግር ምክንያት፡፡ ራሳቸውን ከዘመኑ ጋር ማስኬድ አቅቷቸዋል ማለት ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በዘር፣ በፖለቲካ፣ በሃይማኖና በመሰል ምክንያቶች ልዩነቱ ሰፊ ነው፡፡ ማን ነበር፣ ‹‹ኢትዮጵያውያኑ አሜሪካ ገቡ እንጂ፣ አሜሪካ ውስጣቸው አልገባችም፤›› ያለው፡፡ በጣም ያሳዝናል፡፡

ሰሞኑን የታሰሩ ጦማሪያን፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች እስረኞች በመፈታታቸው እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ አገሬ እስር ቤት እንድትሆን ከማይፈልጉ ኢትዮጵያዊያን አንዱ ነኝ፡፡ መንግሥት ለእስር ከሚቸኩል ይልቅ ለማስተማር ቢተጋ እመርጣለሁ፡፡ ሕግ ጥፋተኛን ማረሚያ እንጂ መቅጫ እንዳይሆን በነካ እጅ የታሰሩትን በሙሉ ፈቶ እፎይ እንበል፡፡ ለታሳሪዎቹም ሆነ ለቤተሰቦች እንዲሁም ለአገር እረፍት ነው፡፡ የዳያስፖራ ወገኖቻችን ‹በትግላችን ነፃ እንዲወጡ አደረግን› የሚሉት ቀልድ ግን ይደብራል፡፡ ከአትላንቲክ ማዶ ሆኖ ፉከራ የተባለ ዕቁብ ስለሆነ ዝም በሉ፡፡

(አ.ብ፣ ከገርጂ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...