Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበወረዳዎች የተንሰራፋውን ችግር የሚመረምር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቋመ

በወረዳዎች የተንሰራፋውን ችግር የሚመረምር ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቋመ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ወረዳዎች በሕግ የመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸው ቢሆንም፣ በተለያዩ  የኅብረተሰብ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እየሰጡ ባለመሆናቸው የተፈጠረውን ችግር የሚመረምር የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቋመ፡፡

የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ በከተማው በሚገኙ 116 ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ሕግጋትንና መዋቅሮችን መመርመር ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ ያሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይተነትናል ተብሏል፡፡ ይህንን ሥራ እስከ 2008 ዓ.ም. አጋማሽ ድረስ በማጠናቀቅ ለከተማው አስተዳደር ካቢኔ የውሳኔ ሐሳብ እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡

ይህ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የሚቋቋመው በከተማው አቅም ግንባታ ቢሮ ሥር ሲሆን፣ የአቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ይስሃቅ ግርማይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኅብረተሰብ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመፍታት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱን ማቋቋም አስፈልጓል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

“ወረዳ ውሳኔ እንዳይሰጥ አስረው የያዙ ችግሮች ምንድን ናቸው? የሚለውን ጉዳይ ይመረምራል፤” የሚሉት አቶ ይስሃቅ፣ “ወረዳዎች ሥልጣን እያላቸው ሊሠሩ ያልቻሉት ለምንድነው? የሚለው ጉዳይ ይታያል፤” በማለት ተናግረዋል፡፡

ሙስናን ለመቅረፍና መልካም አስተዳደር ለማስፈን የሚያስችል ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግም አቶ ይስሃቅ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሉ መሥሪያ ቤቶች 78 ሺሕ ሠራተኞች አሉ፡፡ ይህ የሠራተኛ ቁጥር የአስተዳደሩ መዋቅር ከሚፈልገው 66 በመቶ ብቻ ነው፡፡ የተቀረው 34 በመቶ የሚሆነው የአስተዳደሩ መዋቅር የሚፈልገውን ‹ፕሮፌሽናል› ሠራተኛ አላገኘም ተብሏል፡፡

በተለይ የወረዳ መዋቅሮች ያን ያህል የሠራተኛ እጥረት አለባቸው ባይባልም፣ ያለው የሰው ኃይልም ውሳኔ በመስጠት በኩል ደካማ ነው ተብሏል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በተዋረድ ለወረዳዎች የመወሰን ሥልጣን ቢሰጥም፣ ወረዳዎች ግን አብዛኛዎቹን ጉዳዮች ወደ ክፍለ ከተማ ብሎም ወደ ማዕከል በመግፋት ኅብረተሰቡን እያጉላሉ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የአቅምና የብቃት ማነስ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በወረዳዎች ሙስና መንሰራፋቱ እየተነገረ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡ ባገኘው መድረክ በተለይ ወረዳዎችንና ክፍላተ ከተሞችን በመውቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በሒደት እየጨመረ ያለውን የኅብረተሰቡን ቅሬታ በመፍታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጉዳዩን እየመረመረ የመፍትሔ ሐሳብ የሚያመነጭ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት እንዲቋቋም ወስኗል፡፡ አቶ ይስሃቅ እንዳሉት፣ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ በሰው ኃይል እየተደራጀ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...