Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቻይና ኩባንያዎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ፎረም ተቋቋመ

የቻይና ኩባንያዎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ፎረም ተቋቋመ

ቀን:

  • ኩባንያዎቹ በኃላፊዎቻቸው ላይ የሚወጣ የእስር ትዕዛዝ አሳስቧቸዋል

በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንት ሥራዎች የተሰማሩ የቻይና ኩባንያዎች የሚገጥሟቸውን ችግሮች በተደራጀ መንገድ ለመፍታት የምክክር መድረክ (ፎረም) መቋቋሙን፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ እንደሚጠቁመው፣ በኢትዮጵያ 1,200 የቻይና ኩባንያዎች ተመዝግበው ከእነዚህ ውስጥ 700 ያህሉ በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ጉልህ ሥፍራ የያዙ የቻይና ኩባንያዎች በተደጋጋሚ የሚያነሷቸው ችግሮች አሉ፡፡

እነዚህ ኩባንያዎች በሥራ ላይ የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት በተንጠባጠበ መንገድ በየጊዜው ወደ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የሚሄዱ ሲሆን፣ ይህም ከጊዜ አጠቃቀም አንፃር ችግሮች እንዳሉበት ተመልክቷል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ሥራዎች በገለጸበት ሪፖርት እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ በቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና በሥራ ተቋራጭነት በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ የቻይና ኩባንያዎች፣ በዕለት ተዕለት የሥራ ሒደቶች ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች መፍትሔ ለማግኘት በተናጠል ወደ ሚኒስቴሩ ይሄዳሉ፡፡

‹‹ይኼ አሠራር ከጊዜ አጠቃቀምም ሆነ ከውሳኔ አሰጣጥ ወጥነት አንፃር አግባብነት የሌለው ሆኖ በመገኘቱ፣ አሠራሩን ተቋማዊ በማድረግ ወጥነት ባለው መንገድ ችግሮች የሚፈቱበትን መንገድ ለማመቻቸት ከቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና የንግድ ካውንስለር ጋር በመመካከር፣ ቋሚና አሳታፊ የሆነ የጋራ ምክክር መድረክ እንዲቋቋም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፤›› በማለት የሚኒስቴሩ ሪፖርት ያብራራል፡፡

በምክክር መድረኩ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ ከቻይና ደግሞ የቻይና ኤምባሲ፣ የኤምባሲው የኢኮኖሚና ንግድ ካውንስለር ጽሕፈት ቤት፣ የቻይና ንግድ ምክር ቤትና የቻይና ኮንትራክተሮች ተሳታፊ ናቸው፡፡

ከቻይና ኮንትራክተሮች በኩል ጎልተው ከወጡት ጥያቄዎች መካከል በኩባንያው ኃላፊዎች ላይ የሚደረግ የእስር ትዕዛዝ፣ በአንዳንድ ኩባንያዎች ላይ የሚካሄድ ተደጋጋሚ ኦዲትና የቫት ተመላሽ መዘግየት ተጠቃሽና አሳሳቢ ችግሮች ሆነው መቅረባቸው ተመልክቷል፡፡

ከዓለም ሁለተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ቻይና በኢትዮጵያ ልዩ ፍላጎት ያሏት ሲሆን፣ በርካታ ኩባንያዎች በአምራች ኢንዱስትሪና በኮንስትራክሽን ዘርፎች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...