Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከሚጠበቀው በታች የተጎበኘው የዓለም ዋንጫ ወደ ኬንያ አምርቷል

ከሚጠበቀው በታች የተጎበኘው የዓለም ዋንጫ ወደ ኬንያ አምርቷል

ቀን:

የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ከኮካ ኮላ ኩባንያ ጋር በመተባበር ከ50 በላይ አገሮች እንዲጎበኝ ዕቅድ የተያዘለት የዓለም ዋንጫ የአዲስ አበባ ቆይታውን አጠናቆ ወደ ኬንያ ናይሮቢ አምርቷል፡፡

የካቲት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. በቦይንግ ቢ737 አውሮፕላን ኢትዮጵያ የገባው የዓለም ዋንጫ በአዲስ አበባ ቆይታው ከሚጠበቀው በታች ተጎብኝቷል፡፡ ከጉብኝቱ አዘጋጅ ኮሚቴ ለመረዳት እንደተቻለው ከሆነ በስምንት ሺሕ ሰዎች እንዲጎበኝ ዕቅድ ቢያዝለትም በሦስት ሺሕ ሰዎች ብቻ ጉብኝቱ ተወስኗል፡፡

6.142 ኪሎ ግራም እንደሚመዝን የሚነገርለት የዓለም ዋንጫ፣ 75 በመቶ ያህሉ ከንፁህ ወርቅ የተዘጋጀ መሆኑ ይነገራል፡፡ በዚሁ የተነሳም ዋንጫው ሁለት ጊዜ በዘራፊዎች እጅ መግባቱ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ከዚያ በኋለ ለአሸናፊ ቡድኖች እውነተኛ የዓለም ዋንጫ የማይሰጥ ስለመሆኑ ጭምር ይነገራል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአራት ዓመት አንድ ጊዜ 32 ቡድኖች ሰላማዊ የእግር ኳስ ጦርነት ገጥመው፣ ነገር ግን በአንድ ጠንካራ ቡድን ከፍ ብሎ፣ ወዲያው ወደ ክብር ቦታው እንዲመለስ የሚደረገው የዓለም ዋንጫ፣ በመጪው ክረምት በሩሲያ አስተናጋጅነት ከሚከናወነው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በፊት በተመረጡ አገሮች የሚያደርገውን ጉብኝት ይቀጥላል፡፡ ማጠናቀቂያውም ሩሲያ ይሆናል፡፡

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት አድርጎ፣ በሸራተን አዲስና በአዲስ አበባ ሒልተን ለዕይታ የበቃው የዓለም ዋንጫ፣ እንደ ብዙዎቹ እምነት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለዚህ የተመረጡ አገሮች ለእግር ኳሳቸው እንደ ትንሣኤ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ይሁንና የዓለም ዋንጫ በዚህ መልኩ በኢትዮጵያ እንዲጎበኝ መደረጉ የሚደገፍ መሆኑ እንደተጠበቀ፣ በአቀባበል ሥነ ሥርዓት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተደመጡ አስተያየቶችና ንግግሮች ለእውነተኛው የአገሪቱ እግር ኳስ  ትንሣኤ የሚመጥኑ ሊሆኑ እንደሚገባ ጭምር ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ ቃል በተግባር መተርጎም የነዚህ አካላት ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታ እንደሆነም ያምናሉ፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ ምክንያቱን አስመልክቶ፣ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀደምት ከሚባሉ የእግር ኳስ አገሮች አንዷ ከመሆኗም በላይ በተለይም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከመሠረቱ አራት አገሮች በግባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች፡፡ ይህ የአገሪቱ የእግር ኳስ ታሪክ ‹‹ነበር›› ከሚል ማለፍ እንዳልቻለ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ዕድገቱም የኋሊት መሆኑ እንደሚያስቆጫቸው ምሬታቸውን ጭምር ያቀርባሉ፡፡

ካፍ፣ ኢትዮጵያ በ2020 የሚደረገውን የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) እንድታስተናግድ በተመረጠችበት በዚህ ወቅት፣ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሕጋዊ ባለቤት በውል እንደማይታወቅም ይናገራሉ፡፡ ይኼው  የሚያሳስባቸው አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ‹‹ሕግ ይከበር›› በሚል ሽፋን በፌዴሬሽኑ መቋጫ ያጣው የግለሰቦች እሰጣ ገባም ከወዲሁ የመፍትሔ አቅጣጫ ሊቀመጥለት እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...