‹‹የዓድዋ ድል የአፍሪካውያን ሁሉ ድል ነው! ድል የተደረገችውም ኢጣሊያ ብቻ ሳትሆን ከድሉ 11 ዓመት በፊት በተካሄደው የበርሊን ኮንፈረንስ አፍሪካን ለመቀራመት ግብረ አበርና ስም አበር ሆነው የተገኙት አውሮፓውያን ጭምር ናቸው፡፡››
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ታቦ እምቤኪ፣ ዓምና የዓድዋ ድል መታሰቢያ 121ኛ ዓመት በታሪካዊው ገድላዊ ሥፍራ በዓድዋ ከተማ ከሶሎዳ ተራራ ግርጌ ሲከበር የተናገሩት፡፡