Tuesday, June 18, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልለኅትመት የበቃው የአራት ብሔረሰቦች የባህል ሕግ

ለኅትመት የበቃው የአራት ብሔረሰቦች የባህል ሕግ

ቀን:

‹‹እኛ ተማሪዎች ነን፡፡ የአገር በቀል የፍትሕ ሥርዓቶችን (የባህል ሕጎችን) ለማጥናት ወደ ተለያዩ ብሔረሰቦች ስንሄድ ተማሪ ሆነን ለመማር ነው፡፡ በአመቻቾቻችንና በአስተርጓሚዎች አማካይነት ወደ መረጃ ሰጪዎች ስንቀርብ እስኪርቢቶና ነጭ ወረቀት ይዘን ትምህርታችንን እንከታተላለን፤ እንቀስማለን፡፡ በመሆኑም እኛ ተማሪዎች፣ መረጃ ሰጪዎቻችን መምህሮቻችን ናቸው፡፡ . . . በዚህም ተጠቅመን የድራሼ፣ የሞሲዬ፣ የማሾሌና የኩሱሜ ብሔረሰቦች የባህል ሕግ ሥርዓቶችን ከብሔረሰቦቹ የባህል አባቶችና መሪዎች (አስተማሪዎቻችን) ተምረናል፤››

ይህ መንደርደሪያ የሰፈረው በቅርቡ ለኅትመት በበቃው የአራት ብሔረሰቦች የባህል ሕግ ሥርዓት መጽሐፍ ላይ ነው፡፡ በአቶ አብዱልፈታህ አብደላህ አዘጋጅነት በአቶ መሰለ ማሞ አስተባባሪነት የታተመው መጽሐፍ ‹‹የድራሼ ወረዳ ሕዝቦች የባህል ሕግ ሥርዓት›› ሲባል በደቡብ ክልል በሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን በድራሼ ወረዳ የሚገኙት አራቱ ብሔረሰቦች የባህል ሕግ ሥርዓት በስፋት ቀርቦበታል፡፡

የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓቶችና ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልፈታህ አብደላህ በመልዕክታቸው እንደገለጹት፣ እያንዳንዱ የባህል ሕግ ሥርዓት የራሱ አዲስና ልዩ ባህሪ እንደሚገኝበት ከአራቱ ብሔረሰቦች የባህል ሕግ ሥርዓቶችም አያሌ አዳዲስና አስደሳች ጭብጦች ተገኝቶበታል፡፡ በተለይም የዳማ (በድራሼና በሞሲዬ)፣ የቲቲባ (በማሾሌ)፣ የሩማ (በኩሱሜ) የአካባቢያዊ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓቶች፣ የጎሳዎች የውስጥ አስተዳደርና የዳኝነት ሥርዓት፣ የማኅበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ሕይወት ልማት ባህላዊ ተቋማት ብዛትና ዓይነት፣ ለተፈጥሮ ሀብቶች ጥበቃና እንክብካቤ የሚረዱ እሴቶች በስፋት ከባህል ሕጎቹ ተገኝቷል፡፡ በተለይም የመሬት ለምነትንና እርጥባማነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ  ሳይንሳዊና ባህላዊ ዕውቀቶች በዚህ ጥናት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እንደዚሁም የአስተዳደር ወይም የመንግሥት ሥልጣንን የማከፋፈልና ከፌዴራሊዝም ሥርዓት ጋር የሚዛመዱ ባህላዊ እሴቶችም ይገኙበታል፡፡

- Advertisement -

ባለ 550 ገጽ የቀረበው መጽሐፍ በአራት ዋና ዋና ክፍሎችና ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፣ አራቱ ብሔረሰቦች (ድራሼ፣ ሞሲዬ፣ ማሾሌና ኩሱሜ) በቅደም ተከተል እያንዳንዳቸው አንዳንድ ክፍል ይዘዋል፡፡ እያንዳንዱ የባህል ሕግ ሥርዓት ደግሞ በብዙ ምዕራፎች ተከፋፍሏል፡፡ 144 ባለቀለም ፎቶዎችንም ይዟል፡፡

ከድራሼ ወረዳ የባህል፣ የቱሪዝምና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጋር በመሆን ያሳተመው የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓቶች ማዕከል የአገር አቀፍ የፍትሕ ሥርዓቶችን ለማጥናት፣ ለማልማትና ለማስተዋወቅ የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን፣ ሥራ ከጀመረ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ የአዊ፣ የሲዳማ፣ የጉጂ-ኦሮሞ፣ የሐረሪ፣ የዋግ-ኽምራ፣ የወለኔ፣ የኮንሶ፣ የአፋር፣ የኮሬ፣ የቡርጂ የባህል ሕግ ሥርዓቶችን በተለያዩ ደረጃዎች ጥናት ማካሄዱ ተገልጿል፡፡ የወለኔ፣ የኮንሶና የኮሬ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የባህል ሕግ ሥርዓቶችን በመጽሐፍ መልክ ለኅትመት አብቅቷል፡፡

የሐረሪ፣ የአፋርና የዋግ ኽምራ ብሔረሰቦች የባህል ሕግ ሥርዓቶችንም ለማሳተም በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የሌሎችም ብሔረሰቦችና ጥናቶች እንዲካሄዱ፣ የተጠኑት እንዲታተሙ ከሚመለከታቸው ወገኖች ጋር ሁሉ ለመሥራት በጥረት ላይ እንደሚገኙ ሥራ አስኪያጁ አቶ አብዱልፈታህ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...