Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልዓመታዊ ኢትዮ አፍሪካ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ

ዓመታዊ ኢትዮ አፍሪካ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ

ቀን:

ባህላዊ ሙዚቃና ዳንኪራ የቁንጅና ውድድርና የጎዳና ትርዒት ባዛርና ኤግዚቢሽን የተካተቱበት ዓመታዊ ዓለም አቀፍ ክብረ በዓል በመጪው ግንቦት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡ መጠርያው ‹‹ኢትዮአፍሪካ ካርኒቫል›› ይሰኛል፡፡

የቱሪስቶች ፍሰት እንዲጨምር ያደርጋል የተባለውን ‹‹ኢትዮ አፍሪካ ካርኒቫል›› ሐሳብን ያመነጨው አይጂ ኢንተርቴይመንት ሲሆን ስለክብረ በዓሉ ምንነት፣ ዓላማና ይዘት አስመልክቶ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅትና ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር በመሆን የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. መግለጫ ሰጥቶ ነበር፡፡

ከግንቦት 19 ቀን ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚዘልቀው ክብረ በዓል፣ ከሚኖሩት ሁነቶች አንዱ ‹‹ወይዘሪት ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት” በሚል መጠርያ የሚካሄደው የቁንጅና ውድድር ነው፡፡

- Advertisement -

በመግለጫው እንደተወሳው፣ ከሁሉም ክልሎችና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች ባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ጋር በመተባበር በየከተሞቹ በሚካሄደው የቁንጅና ውድድር በሚለዩት አምስት አሸናፊዎች መካከል የማጠናቀቂያ ውድድሩ በአዲስ አበባ ተደርጎ አሸናፊዋ ‹‹ወይዘሪት ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ›› የሚል ስያሜ ይሰጣታል፡፡

ኢትዮ ካርኒቫል፣ አዲሱ የኢትዮጵያ ቱሪዝም መለያ (ብራንድ) በስፋት ለማስተዋወቅ፣ ማኅበረሰባዊና ባህላዊ እሴቶችንም ለቱሪስቶች ለማቅረብ ዓላማን የሰነቀ መሆኑ ተወስቷል፡፡

በተለይም ከዚህ ቀደም ለባርካታ ዘመናት የኢትዮጵያ ቱሪዝም መለያ የነበረውን የ13 ወራት ጸጋ በ‹‹ምድረ ቀደምት›› ከመቀየሩ ጋር በተያያዘ የመጠሪያውን ምንነትና ትርጓሜ፣ እንዲሁም አገራዊ ፋይዳውን ለማስገንዘብና ዓለም አቀፋዊ መግባባት ለመፍጠር ሰፊ ዕድል እንዳለው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮሐንስ ጥላሁን አስረድተዋል፡፡

አቶ ዮሐንስ አክለው እንደተናገሩት፣ በካርኒቫሉ ከአገር ውስጥ ተሳታፊዎች በተጨማሪ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ተሳታፊዎች በማምጣት ዝግጅቱን አፍሪካዊ ውበት እንዲኖረው እንጥራለን ብለዋል፡፡

በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከወይዘሪት ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ የቁንጅና ውድድር በተጨማሪ በካሪኒቫሉ የመንገድ ዳንስ፣ ባህላዊ፣ ሙዚቃ፣ ባህላዊ አልባሳት ትርዒትና ከአሥር ሺሕ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት የእግር ጉዞ እንደተዘጋጀ ተብራርቷል፡፡

በካርኒቫሉ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ የንግዱ ማኅበረሰብ፣ በቱሪዝም ዘርፍ የተሠማሩ ድርጅቶች ያሳትፋልም ተብሏል፡፡

ካርኒቫሉ ከዘንድሮ በኋላ በየዓመቱ የቱሪስቶች የፍሰት ወቅት በሆነው ጥር ወር ላይ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ወደ አገር የሚገቡ ቱሪስቶች በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች የቆየ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙና አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ እንዲያድግ ያደርጋልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመድረኩ አፍሪካውያን እርስ በርሳቸው የተለያዩ ባህላዊ እሴታቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ የሚያቀርቡበት፣ ባህላቸውን፣ ወጋቸውንና አስተሳሰባቸውን ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ እንደሚሆን እምነታቸው መሆኑን አቶ ይስሐቅ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

እንደ አዘጋጆቹ አገላለጽ፣ በብራዚል ሪዮ ዲጂዴነሮ ከተማ የሳንባ ዳንስን መሠረት አድርጎ በየዓመቱ የሚካሄደውን ካርኒቫል ለመሳተፍ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች ይተማሉ፡፡ በውጤቱም ብራዚል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማግኘት ተጠቃሚ መሆኗ ይነገራል፡፡ ይኼን የብራዚል መልካም ተሞክሮ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ይጠበቃል ብለዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...