Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ይበል የሚያሰኙ ጅምሮች

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ይበል የሚያሰኙ ጅምሮች

ቀን:

የስፖርት ጋዜጠኞች፣ አርታኢዎች፣ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችና የተለያዩ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ኃላፊዎች የተሳተፉበት ሴሚናር ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዳማ ሪፊት ቫሊ ሆቴል ተከናውኗል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባዘጋጀው የሁለት ቀን ሴሚናር ከአገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች የታደሙ ኃላፊዎችና የስፖርት መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቷቸው በአገሪቱ እየተዘወተሩ ለሚገኙ ስፖርቶች ዕድገት “የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ምን ያህል ተወጥተዋል?” በሚል በቀረቡ አንኳር ነጥቦች ላይ ይበል የሚያሰኝ ውይይቶችንና ክርክሮችን አድርገዋል፡፡ መድረኩን በማመቻቸት ትልቁን ኃላፊነት የወሰደው ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጅምሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልበት ተጠይቋል፡፡

ኦሊምፒክና የኦሊምፒክ ፅንሰ ሐሳቦች ላይ መነሻውን ባደረገው ሴሚናር በአገሪቱ ገነው ከወጡ እግር ኳስና አትሌቲክስ ባሻገር ሌሎች ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና የሚመሯቸው ስፖርቶች ከስፖርቱ መገናኛ ብዙኃን ጋር ያላቸው ቁርኝት እጅግ የላላ መሆኑ ለመከራከሪያነት ከቀረቡት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የተዘጋጀው መድረክ ሁሌም አንዱ በሌላው ጣት በመጠነቋቆል ሲተቻቹ የቆዩት በጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፊት ለፊት መገናኘታቸው በችግሮቹ ዙሪያ ግልጽ ውይይት እንዲደረግ የራሱን ድርሻ ተወጥቷል፡፡

የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ኃላፊዎች የአገሪቱ የስፖርት መገናኛ ብዙኃን የመንግሥትም ሆነ የግሉ ዘርፍ ከአገር ውስጥ ስፖርቶች ለእግር ኳስና አትሌቲክስ በመጠኑ ቢሆን ትኩረት ቢሰጡም፣ የሙሉ ጊዜ ሥራቸውን ግን ለአውሮፓ እግር ኳስ መሆኑ ለሁሉም ስፖርቶች ውድቀት ተጠያቂ ተደርገው ሊወሰዱ እንደሚገባ  ሲያመለክቱ በስፖርት ሚዲያው በኩል ደግሞ እንደተባለው በአገሪቱ ከእግር ኳስና አትሌቲክስ በስተቀር የሌሎቹ ስፖርቶች ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በዓመት አንድ ጊዜ ከሚያከናውኗቸው ጠቅላላ ጉባኤ በዘለለ የስፖርት መገናኛ ብዙኃኑን ሊጋብዝ የሚችል መሬት የወረደ የዕቅድ መርሐ ግብር እንኳ የሌላቸው መሆኑ መጠቀሱ ውይይት ምን ያሀል ግልጽነት የተሞላበት እንደነበረ አመላክቷል፡፡

የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት አገር አቀፍ ፌዴሬሽኖች የድርሻቸውን የስፖርት መገናኛ ብዙኃኑም በተመሳሳይ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት መግባባት ላይ የተደረሰ ከመሆኑ ባሻገር ለዚህ መድረክ መፈጠር የበኩሉን ድርሻ የተወጣው ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በበኩሉ፣ በተለይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች መረጃን በአግባቡ ያደርሱ ዘንድ ከዘመናዊ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎች ጋር አብረው እንዲራመዱ በጀት ከመመደብ ጀምሮ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ታምራት በቀለ በኩል ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡

ኃላፊው አብዛኞቹ የስፖርት መገናኛ ብዙኃንና ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ጥሩ የሚባል አለመሆኑን ገልጸው፣ ሁለቱ አካላት ሳይተዋወቁ አንዱ ሌላውን ሲወቅስና ሲከስ መመልከት የዕለት ተዕለት አጀንዳ ሆኖ መቆየቱን ጭምር ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ግን በዚህ መልኩ መቀጠል እንደማይቻልም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡   

 

 

 

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...