Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቡድን 77 አገሮች ዓለም አቀፍ የታክስ ተቋም እንዲመሠረት የተነሳውን ጥያቄ በመደገፍ ኃያላን...

የቡድን 77 አገሮች ዓለም አቀፍ የታክስ ተቋም እንዲመሠረት የተነሳውን ጥያቄ በመደገፍ ኃያላን አገሮችን ተቃወሙ

ቀን:

ቡድን 77 የሚባሉ ታዳጊ አገሮችና ቻይና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) መዋቅር ውስጥ የሚካተት ዓለም አቀፍ የታክስ ተቋም እንዲመሠረት፣ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ ላይ ያነሱትን ጥያቄ የደገፉ አሥር የሚሆኑ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሲቪክ ማኅበራት፣ የኃያላን መንግሥታት ጥያቄውን ለማድበስበስ እየጣሩ ነው በሚል ተቃውሟቸውን አሰሙ፡፡

በአዲስ አበበ በመካሄድ ላይ በሚገኘው ሦስተኛው ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ እየተካሄደ በሚገኝበት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ውስጥ፣ ሲቪክ ማኅበራቱ ፖስተሮችን በመያዝና ሌሎች ሳቢ ቁሳቁሶችን በመጠቀም ለቡድን 77 አገሮች ድጋፋቸውን ሲሰጡ ተስተውለዋል፡፡

‹‹ዓለም አቀፍ የታክስ ተቋም አሁን›› እንዲሁም ‹‹የታክስ ፍትሕ›› የተሰኙ መፈክሮችን በማስተጋባት፣ በጉባዔው ላይ አሜሪካና ሌሎች ኃያላን የአውሮፓ አገሮች ጥያቄውን በመሸፈን ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው አድርገዋል ብለዋቸዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የታክስ ተቋም ቢመሠረት ከታዳጊ አገሮች በታክስ ማጭበርበሮች ብቻ ድንበር ዘለል ኩባንያዎች፣ በየዓመቱ ከአፍሪካ የሚያወጡትን 100 ቢሊዮን ዶላር ማስቀረት ይችላል የሚል መከራከሪያ የያዘ ወረቀትም በትነዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር አፍሪካ እያጣች ያለችውን እጅግ በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች በመግታት፣ ታዳጊ የአፍሪካ አገሮች የልማት ፋይናንስ ፍላጎታቸውን በራሳቸው መሸፈን ይችላሉ በማለት ይከራከራሉ፡፡

ኦክስፋም፣ ፋይናንሺያል ትራንስፖረንሲ ጥምረት፣ ክርሲቲያን ኤድ፣ አክሽን ኤድ፣ ግሎባል አሊያንስ ፎር ታክስ ጀስቲስ የተወሰኑት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሲቪክ ማኅበራት ናቸው፡፡

በአሜሪካና በሌሎች ኃያላን የአውሮፓ አገሮች እየተሰጠ ያለው ምላሽ ግን፣ በተመድ ሥር ታክስን የተመለከተ ምክር ቤት መኖሩን በመግለጽ ዓለም አቀፍ የታክስ ተቋም አያስፈልግም ይላሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠርና የሀብት ማሸሽን ለመከላከል ድንበር ዘለል የታክስ ኦዲት በአማራጭነት አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በአገሮች የታክስ ስምምነቶች ውስጥ የታክስ ማጭበርበርን የሚከላከል አንቀጽ እንዲገባ በማድረግ፣ ችግሩን መቅረፍ እንደሚቻል ይከራከራሉ፡፡

በሌላ በኩል ታዳጊ አገሮች የታክስ አሰባሰብንና የታክስ መሠረትን ማስፋት እንዲችሉ የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይገልጻሉ፡፡

የእነዚህ ሁለት ተቃራኒ ሐሳቦች የመጨረሻ ውጤት ምን ይሆናል? የሚለው ባይታወቅም፣ ሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ መጨረሻው ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...