Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለከተሞች የውኃ አቅርቦትና ፅዳት የ1.82 ቢሊዮን ብር የብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ

ለከተሞች የውኃ አቅርቦትና ፅዳት የ1.82 ቢሊዮን ብር የብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ

ቀን:

ኢትዮጵያ የትንንሽና የመካከለኛ ከተሞችን የውኃ አቅርቦት ማሻሻልና ፅዳት ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የ1.82 ቢሊዮን ብር (80 ሚሊዮን ዩሮ) የብድርና የዕርዳታ ስምምነቱን ረቡዕ ሐምሌ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል የተፈራረመችው ከፈረንሣይ የልማት ኤጀንሲ፣ ከጣሊያን የልማት ትብብርና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር ነው፡፡

ፕሮጀክቶቹ የተቀረፁት መንግሥት የከተማ የውኃ አቅርቦትንና የፅዳት አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማገዝ ነው፡፡ የፕሮጀክቶቹ ተፈጻሚነት በጥቅሉ ለአገሪቱ ሕዝብ ጤናና የኑሮ ሁኔታ መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሺዴና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ፒም ቫን ባሌኮም ናቸው፡፡

አቶ አህመድ እንዳሉት ኢትዮጵያ ባለፉት ከአሥር በላይ ዓመታት ያስመዘገበችው ሁለት አኀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ብቻም ሳይሆን የዕድገቱ ሁሉን አቀፍም መሆንም ሊተኮርበት ይገባል፡፡ ለሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተሳካ ትግበራ የብድር ስምምነቱ ጠቃሚና አስፈላጊ እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት የውኃ አቅርቦትና ንፅህና ላይ በሚደርግ ኢንቨስትመንት በአገሪቱ ከ120,000 በላይ አባወራዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ኢንቨስትመንቱ በዋተር ሪሶርስ ዴቨሎፕመንት ፈንድ (WRDF) የሚደገፍ ሲሆን፣ ለክልል የውኃ ልማት ባለሥልጣን ተቋማት የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

ከ80 ሚሊዮን ዩሮው 75 ሚሊዮን ዩሮው የረጅም ጊዜ ብድር ሲሆን አምስቱ በድጋፍ መልክ የተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባቱ ውጥን

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል በሦስት ዙር ተካሄዶ በነበረው ጦርነት ምክንያት...

በርካታ ሰዎችን እያጠቁ የሚገኙት የሐሩራማ አካባቢ በሽታዎች

ትኩረት የሚሹ የትሮፒካል /ሐሩራማ በሽታዎች በአብዛኛው ተላላፊ ሲሆኑ፣ በዓይን...

ስለአገር ኢኮኖሚ ማሰብ የነበረባቸው ጭንቅላቶች በማያባሩ ግጭቶች ተነጥቀዋል!

አገራችን ኢትዮጵያ ውጪያዊና ውስጣዊ ፈተናዎቿ መብዛት ብዙ ዋጋ እያስከፈላት...