Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊግሎባል ፈንድ 551 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ከጤና ጥበቃ ጋር ተፈራረመ

  ግሎባል ፈንድ 551 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ከጤና ጥበቃ ጋር ተፈራረመ

  ቀን:

  ግሎባል ፈንድ ኢትዮጵያ ቲቢና ኤችአይቪን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ለምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የሚውል 551 ሚሊዮን ዶላር ለመለገስ ሐሙስ ሐምሌ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ከሰተ ብርሃን አድማሱ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ቀደም ሲል በድጋፍ መልክ የተሰጡ ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለታለመው ዓላማ በማዋል አገሪቱ ማስመስከሯን ገልጸዋል፡፡ የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ማርክ ዳይቡል ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የምትከተለው አዲሱ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሐዊነት ላይ ያተኮረ አካሄድ እንደዚህ ያሉ ድጋፎችን ውጤታማ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡

  ግሎባል ፈንድ ድጋፉን በማስመልከት ስምምነት የተፈራረመው ከጤና ጥበቃ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሲቪል ማኅበራት ኅብረት ጋርም ነው፡፡ ማኅበራቱን በመወከል በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የክርስቲያን በጐ አድራጐትና ልማት ኅብረት (CCRDA) ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ ይህ የገንዘብ ድጋፍ በሚገባ ሥራ ላይ እንደሚውል እንደ ሲቪል ማኅበርና እንደ ልማት አጋርም ከመንግሥት ጋር አብረው እንደሚሠሩ አስታውቀዋል፡፡

  በሌላ በኩል ረቡዕ ሐምሌ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. የገንዘቡ መጠን ባይገለጽም ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ በተለይም በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ተግባራዊ የምታደርገውን የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን ስምምነት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ተፈራርመዋል፡፡

  የጤና ዘርፉ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የአገልግሎት ጥራትና ፍትሐዊነት ላይ እንደሚያተኩር የገለጹት ዶ/ር ከሰተ ብርሃን የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የኅብረተሰብ ተሳትፎ በጤናው ዘርፍ ለተመዘገቡ ጉልህ መሻሻሎች ወሳኝ እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡

  እሳቸው እንደገለጹት የአጭር ጊዜ ግቦች ላይ ብቻ በማተኮር ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ቢቻልም በዘላቂነት የሚያገለግል ሥርዓት መዘርጋት ዋናው ትልቁ ግብ ነው፡፡ ‹‹ዕቀዶቻችሁ በጣም የተጋነኑ ናቸው እየተባለ በተደጋጋሚ አስተያየት ይሰጣል፡፡ ዕቅዶቻችን የተለጠጡ መሆናቸውን እኛም እናውቃለን ነገር ግን ዕቅዶቻችንን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ መሠረቶችና ሥርዓቶች እንዳሉን እናውቃለን፤›› ብለዋል ዶ/ር ከሰተ ብርሃን፡፡

  የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አህመድ ሺዴ ጤና የአገሪቱ አንድ የልማት አጀንዳ፤ የሰብአዊ መብት ጉዳይም እንደሆነ በመጥቀስ ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው ጤናማ ማኅበረሰብ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ‹‹ስለዚህም መንግሥት የልማት አጋሮችን ድጋፍ በመያዝ የሕዝቡን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ጥረቶችን ያደርጋል፤›› ብለዋል፡፡ ሚኒስቴሩም በጤናው ዘርፍ ዕቅድ አወጣጥ የሚኖረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡  

  ስምምነቱ የተደረገው የሦስተኛው የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ በኢትዮጵያ አካል ሆኖ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በተደረገ ዝግጅት ላይ ነበር፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...