Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየደቡብ ጎንደር ዞን መስህቦችን የሚያስተዋውቅ ማውጫ ታተመ

  የደቡብ ጎንደር ዞን መስህቦችን የሚያስተዋውቅ ማውጫ ታተመ

  ቀን:

  ‹‹ሦስት ቅዱሳን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ በመጓዝ ላይ ሳሉ አንዲት ሴትን ከወንዝ ውኃ ቀድታ ስትመጣ ያገኟታል፡፡ ቅዱሳኑ ከተማዋን ስለማያውቋት የከተማዋን ስም ለማወቅ ይህችን ሴት የከተማዋን ስም ጠየቋት፤ ግን መልስ አልሰጥ አለቻቸው፡፡ አንደኛው ‹‹ይች ሴት እብን ናት እንዴ?›› ይላታል፤ በዚያን ጊዜ ታላቁና ብልሁ ሌላኛው አያትና፣ ‹‹እብን ሳትሆን ውብ ናት፣ የሴት ተጋሪና ምላሰኛ ምን ያደርጋል?›› ብሎ ለአንደኛው ይነገረዋል፤ በዚህ ጊዜ ግእዝን ከአማርኛ ለይተው የማያውቁ እብናት ብለው አወጡላት፤ ትርጉምም ደንጋ ማለት ነው፤ ነገር ግን አጠራሩ ውብናት ነው ይላሉ፡፡››

  ይህን ትረካ የያዘው ሰሞኑን ለሥርጭት የበቃው ‹‹የደቡብ ጎንደር ዞን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማውጫ›› ነው፡፡ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በደቡብ ጎንደር ዞን ስለሚገኙ ልዩ ልዩ መዳረሻዎችና ሀብቶች በተመለከተ በሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን የታተመው ማውጫ ከተመለከታቸው አንዱ በዞኑ የሚገኘው እብናት ወረዳ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ 744 ኪሎ ሜትር፣ ከባህርዳር 122 ኪሎ ሜትር፣ ከደብረታቦር 109 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ለሚገኘው የእብናት ወረዳና ሌሎች 10 ወረዳዎችና ሁለት ከተሞች ማኅበራዊና ባህላዊ፣ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ገጽታዎች ከመንፈሳዊ ሕይወት ጋር ተዘርዝሮበታል፡፡

  ደቡብ ጎንደር ዞን በኢትዮጵያ በርዝመቱ ሦስተኛ ተራ የሆነው ጉና ተራራ (4231 ሜትር) እና የዓባይ አንጋፋ ገባር ወንዞች የሆኑት የርብና የጉማራ መነሻ ነው፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በቤንዚንና ነጭ ናፍጣ ላይ ጭማሪ ተደረገ

  ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ...

  ‹‹ለሰላምና ለዕርቅ መሸነፍ የለብንም›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

  የሰው ልጅ ጠብን በዕርቅ፣ በደልን በይቅርታ፣ ድህነትን በልማት፣ ክህደትን...

  መፍትሔ አልባ ጉዞ የትም አያደርስም!

  ኢትዮጵያ ችግሮቿን የሚቀርፉ አገር በቀል መፍትሔዎች ላይ ማተኮር ይኖርባታል፡፡...

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...