Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትክብረወሰኖችን መስበር ባህሉ ያደረገ ቤተሰብ

  ክብረወሰኖችን መስበር ባህሉ ያደረገ ቤተሰብ

  ቀን:

  የፋና ወጊዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉን እግር የተከተሉ ከዋክብት ከበቆጂ ገጠራማ መንደሮች መፍለቅ ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ አዳዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ክብራቸው ሆኖ እየሰባበሩ ሲያስፈነጥዙን ኖረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለክብሯ የከበሩ አትሌቶች እንዳላጣች ዛሬም በዓለም መድረክ ክብር ለብሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ የእግር ምህተሃተኞች የሚያስመዘግቧቸው አንፀባራቂ ድሎች ይመሰክራሉ፡፡

  እህታሞቹ ጥሩነሽ ዲባባና ገንዘቤ ዲባባ እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በዘርፉ ትልቁን ቦታ ከያዙት ተጠቃሾች ሆነዋል፡፡ የእንስቶቹ ቤተሰብ በሁለቱ ብቻም ሳይወሰን እነ እጅጋየሁ ዲባባ፣ የሁሉ ዲባባና ምንም እንኳ እንደ እህቶቹ ሊጠቀስ የሚችል ታሪክ ላይ ባይደርስም ደረጀ ዲባባ በአትሌቲክሱ መስክ በመሰለፍ የአገሪቱን ሰንደቅ ከፍ ለማድረግ ከተጉ ግንባር ቀደሞቹ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡

  ከሰሞኑ የዓለም መነጋሪያ የሆነው ክስተት በሞናኮ ከተማ ተከናውኗል፡፡ ከታላቅ እህቷ በውርስ የተሰጣት እስኪመስል በድል በድል የሰነበተችው ገንዘቤ ዲባባ በ1,500 ሜትር ርቀት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ሆናለች፡፡

  እንደ ሰሞኑ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ገንዘቤ ዲባባ የላውረን  የዓለም የዓመቱ ምርጥ ሴት ስፖርተኛ መሆኗ ይፋ ሆኗል፡፡ አትሌቷ ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ በተሳተፈችባቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ተደጋጋሚ ክብረ ወሰኖችን በመሰባበር የግሏ ከማድረግ አልፋ በአትሌቲክሱ ዓለም ትልቅ ቦታ እንድታገኝ አስችሏታል፡፡

  የ22 ዓመቷ ገንዘቤ ዲባባ፣ ባለፈው የውድድር ዓመት መጀመርያ በስቶክሆልም 1,500 የቤት ውስጥ ውድድር፣ ከዚያም ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ3,000 እና የሁለት ማይልስ የቤት ውስጥ ውድድር አዳዲስ የዓለም ክብረወሰኖችን በማስመዝገብ አንቱታን ማግኘቷ ይታወሳል፡፡ እየተገባደደ በሚገኘውም የውድድር ዓመት በተመሳሳይ በማራኪ ድል ለማጠናቀቅ እየተንደረደረች ያለችው ገንዘቤ፣ በስቶክሆልም በተከናወነው የዓለም የቤት ውስጥ 5,000 ሜትር አሸናፊ መሆኗ የስኬቷ አንዱ አካል ነው፡፡ አትሌቷ በታላቅ እህቷ ጥሩነሽ ዲባባ ስም ለሰባት ዓመታት ተይዞ የቆየውን የቦታውን ክብረ ወሰን ለመስበር ከፍተኛ ትግል አድርጋ ሳይሳካላት ቀርቷል፡፡ ይሁንና ድል የለመዱት የገንዘቤ እግሮች በዚህ ተስፋ ሳይቆርጡ ፓሪስ ላይ በተደረገው ዳይመንድ ሊግ አሸናፊ ሆናለች፡፡ ቀጥላም በባርሴሎናና ሌሎችም ከተሞች ባደረገቻቸው የተለያዩ ውድድሮች አይበገሬነቷን እንዳስጠበቀች መዝለቅ ችላለች፡፡

  የአትሌቷ ውጤታማነት ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ እየናኘ ባለበት በዚህ ዓመት በሞናኮ ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. በተከናወነው አሥረኛው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በ1,500 ሜትር እንደገና የዓለም አዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን የበቃችበትን ድል አስመዘገበች፡፡ በጃፓናዊቷ ዩኒዥያን ከሃያ ዓመታት በላይ በ3 ደቂቃ 50 ነጥብ፣ 46 ሰከንድ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን ወደ 3 ደቂቃ 50፡07 ሰከንድ አጠናቃ ክብረወሰኑን በእጇ አስገብታለች፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...