‹‹ሳይኪና ኪዩፒድ›› እና ‹‹የቋንቋ መሠረታውያን›› ለንባብ በቁ
‹‹ሳይኪና ኪዩፒድ›› እና ‹‹የቋንቋ መሠረታውያን›› በቅርቡ ለንባብ የበቁ የአብነት ስሜ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ‹‹ሳይኪና ኪዮፒድ›› አሥር ተረቶች፣ አራት መቶ እንቆቅልሾችና አንድ የእንግሊዝኛ ልቦለድ የያዘ መጽሐፍ ነወ፡፡ ጸሐፊው በተለያየ ወቅት ያነበባቸው እንዲሁም በልዩ ልዩ መድረኮች ላይ የተረካቸውን ታሪኮች የያዘው መጽሐፉ 411 ገጾች አሉት፡፡ ጸሐፊው በመግቢያው ላይ እንደጠቀሰው፣ በተለይ የመጽሐፉ መጠሪያ የሆነው ታሪክ ከዋናው በተለየ ኢትዮጵያዊ ቀለም ሰጥቶታል፡፡ ‹‹ተወዳጅ ተረቶች ለኢትዮጵያ ልጆች›› በሚል መሪ ቃል የሚጀምረው መጽሐፉ በ90 ብር ከ99 ሣንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ሌላው የአብነት መጽሐፍ ‹‹የቋንቋ መሠረታውያን›› ጋዜጠኞች፣ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እንዲሁም በቋንቋ፣ በፎክሎር፣ በባህል፣ በታሪክና በትርጉም ዙሪያ ለሚሠሩ ግለሰቦች ጠቀሜታ እንደሚኖረው በመግቢያው ተጠቁሟል፡፡ በ14 ምዕራፎች ቋንቋ ነክ ርእሰ ጉዳዮችን የሚዳስሰው መጽሐፍ 407 ገጾች አሉት፡፡ በ90 ብር ከ99 ሣንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
********
የመጽሐፍ ምርቃት
‹‹ባቡሩ ሲመጣ›› የተሰኘው የጋዜጠኛና ደራሲ አንተነህ ይግዛው የአጫጭር ልቦለዶች መድበል ሐምሌ 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በ11፡30 በኢትዮጵያ ሆቴል ይመረቃል፡፡ 14 አጫጭር ልቦለዶች የያዘው መጽሐፉ 210 ገጾች አሉት፡፡ በ60 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት፣ በአዲስ ዘመን ጋዜጣና በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሠርቷል፡፡ የመጀመርያ መጽሐፉ ‹‹መልስ አዳኝ›› በ2003 ዓ.ም. ለንባብ መብቃቱ ይታወሳል፡፡