‹‹ቅንጣት››
‹‹ቅንጣት የኔዎቹ ኖቭሌቶች ‘ሞገደኛው ነውጤ እና ሌሎች’›› የተሰኘው የአበራ ለማ መድበል ለንባብ በቅቷል፡፡ መድበሉ አራት ኖቭሌቶች የያዘ ነው፡፡ ደራሲው በመግቢያው ላይ እንዳሰፈረው ኖቭሌት በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ እየታወቀ የመጣ የአጻጻፍ ዘዬ ነው፡፡ ኖቭሌት ከኖቪላና ቤሳ ልቦለድ በበለጠ ጥበባዊ ክህሎት የሚታይበት እንደሆነ ደራሲው አትቷል፡፡ በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ኖቬላና ቤሳ ልቦለዶች ቢዘወተሩም ኖቭሌት አልተለመደም፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም ‹‹መቆያ›› በተባለ መጽሐፉ ያካተተው ተደናቂ ሥራው ‹‹ሞገደኛው ነውጤ›› በአዲሱ መድበሉ ዳግም አሳትሞታል፡፡ አግዮስ ኅትመትና ጠቅላላ ንግድ ሥራ ያሳተመው ቅንጣት ዋጋው 70 ብር ነው፡፡
*********
የአባትና የልጅ ዐውደ ርዕይ
ዝግጅት – ‹‹አባትና ልጅ›› በሚል ሠዓሊ ለማ ጉያና ልጃቸው ሠዓሊት ነፃነት ለማ በጋራ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ያዘጋጁ ሲሆን፣ ለ20 ቀናት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
ቀን – ሐምሌ 18 ቀን 2007 ዓ.ም.
ሰዓት – ከረፋዱ 5፡00
ቦታ – የኦሮሚያ ባህል ማዕከል
አዘጋጅ – ነፃ አርት ስቱዲዮ