Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየግል ትምህርት ቤቶችን የክፍያ ተመን ለመቆጣጠር ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

የግል ትምህርት ቤቶችን የክፍያ ተመን ለመቆጣጠር ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ በግል ትምህርት ቤቶች ለትምህርትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚጠየቁ ተጨማሪ ክፍያዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ መመርያ መዘጋጀቱን፣ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው በከተማው ውስጥ በሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ባካሄደው የናሙና ጥናት መሠረት፣ 194 ትምህርት ቤቶች ተገቢ ያልሆኑና የተጋነኑ ክፍያዎች የሚያስከፍሉ በመሆናቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብሏል፡፡

በትምህርት ቢሮው የትምህርት ጥራት ቁጥጥርና ኤንስፔክሽን ኃላፊ አቶ ማስረሻ ዘሪሁን ለሪፖርተር እንደለጹት፣ የግል ትምህርት ቤቶች ከምዝገባ ጀምሮ ለትምህርት አገልግሎት ምንም ዓይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖራቸው የተጋነነ ክፍያ እያስከፈሉ እንደሚገኙ በጥናት ተረጋግጧል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አብዛኛዎቹ ወላጆች በከፍተኛ ጫና ምክንያት የሚያቀርቡት ቅሬታ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱን አክለዋል፡፡ የትምህርት ቤቶችን የተጋነኑና አላስፈላጊ ክፍያዎችን ለመቆጣጠር ትምህርት ቢሮው ከንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ጋር በመሆን መመርያ ለማውጣት መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡ በረቂቅ መመርያው ላይ ከተማሪ ወላጆች፣ ከትምህርት ቤቶችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉንና ወደ ተግባር ለመግባት የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለረቂቅ መመርያው ዝግጅት እንደ ግብዓት ያገለገለው በትምህርት ቢሮው የተሠራው ጥናት መሆኑን የገለጹት አቶ ማስረሻ፣ ብዛት ያላቸው ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ብቻ እስከ 1,000 ብር ድረስ እንደሚጠይቁም አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ትምህርት ቤቶቹ ከዋና ዓላማቸው ውጪ ያላግባብ ገንዘብ በመሰብሰብ በወላጆች ላይ ጫና እያሳደሩ ነው ብለዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ጥራታቸው በመንግሥት ሳይረጋገጥ በራሳቸው ፍላጎት መጻሕፍት በማሳተም በውድ ዋጋ መሸጥ፣ የተማሪዎች ዩኒፎርምና የስፖርት ትጥቅ በግድ በመሸጥ፣ እንዲሁም ለተለያዩ በዓላት በማለት ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በዚህ ሳቢያ በከተማዋ ከ1,671 የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለ194 ማስጠንቀቂያ የተሰጠ መሆኑን፣ ከአሥር በላይ ለሚሆኑት በድጋሚ ቢሮው ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች ከዚህ በኋላ ችግር ቢፈጥሩ ትምህርት ቢሮው ዕውቅናቸውን እንደሚነጥቅና እንደሚዘጋቸው አስጠንቅቀዋል፡፡

ትምህርት ቤቶችን መዝጋት ቀላል እንዳልሆነም ኃላፊው ሲያስረዱ፣ ‹‹ትምህርት ቤቶችን አጠፋችሁ ብሎ እንደ ሱቅ ለማሸግ መሞከር ቀላል አይደለም፡፡ ተነስቶ መዝጋቱም የራሱ ችግር ስላለው ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን የሕዝብ ጥቅም ከመንካቱም በላይ ጎጂነቱ ከታመነበት የማይታሸጉበት ምክንያት የለም፤›› ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ትምህርት ቤቶቹ በትምህርት ቢሮው ግምገማና ጥናት ላይ ቅሬታቸውን ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡ በተለይ ሦስት መሠረታዊ ችግሮች እንዳሉባቸው በመግለጽ የትምህርት ቢሮው መፍትሔ እንዲሰጥባቸው ይጠይቃሉ፡፡ ለመምህራንና ለሠራተኞች የሚከፈል ወጪ እየጨመረ መምጣት፣ ከፍተኛ የቤትና የሕንፃ ኪራይ፣ እንዲሁም የጽሕፈት መሣሪያዎች ዋጋ እየናረ መምጣት ትኩረት እንደሚያሻው ይጠይቃሉ፡፡ መንግሥት ይህንን የትምህርት ቤቶቹን ስሞታ ቢቀበለውም፣ ጥቂት የማይባሉ ትምህርት ቤቶች ግን ከሚገባው በላይ ክፍያ እንደሚጠይቁ የትምህርት ቢሮው አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች መንግሥት ለትምህርት ዘርፍ ማበረታቻ አለመስጠቱን ይተቻሉ፡፡ የትምህርት መሣሪያዎችን ከቀረጥ ነፃ ከማስገባት ጀምሮ የሕንፃ መገንቢያ ቦታ በሕጉ መሠረት የሊዝ ቅድሚያ በመስጠት አለማበረታታቱንም ይገልጻሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...