Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ‹‹ልዩ ሰዎች ልዩ ዕድል ያገኛሉ››

‹‹ልዩ ሰዎች ልዩ ዕድል ያገኛሉ››

ቀን:

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እሑድ አመሻሽ (ሐምሌ 19 ቀን 2007 ዓ.ም.)  አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ የተለያዩ ስብሰባዎችን ተካፍለዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ስላደረጉት ውይይት ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል፡፡

በማግስቱ ሰኞ ዕለት ኦባማ 3.2 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረችውን የሉሲን ቅሪተ አካል የጎበኙት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ከተደረገላቸው እራት ግብዣ አስቀድሞ ነበር፡፡

በከፍተኛ የደኅንነት ጥበቃ በጥንቃቄና በምስጢር ከብሔራዊ ሙዚየም ወደ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የተወሰደውን የሉሲን ቅሪተ አካል ኦባማ በተመለከቱበት ቅጽበት ‹‹በጣም ይገርማል›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር አሚን አብዱልቃድር በተገኙበት ሉሲን ያስጎበኟቸው በካሊፎርኒያ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ የአንትሮፖሎጂ ሲኒየር ኪውሬተርና የፕሬዚዳንቱ ቱር ጋይድ ዶ/ር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ ናቸው፡፡

ኦባማ ሉሲን ማየት ብቻ ሳይሆን ከቅሪተ አካሉ አጥንቶች አንዱን እንዲዳስሱ ተጋብዘው ነክተውታል፡፡ ቅሪተ አካሉን ከሚፈቀድላቸው ተመራማሪዎች በስተቀር ማንም እንዳይነካ ቢደነገግም የፕሬዚዳንቱ መነካካት ግን በብዙዎች ዘንድ ጥያቄ አስነስቷል፡፡

 

ዶ/ር ዘረሰናይ እንደተናገሩት፣ ሉሲ በከፍተኛ ጥበቃ ሥር ከምትቀመጥበት ሙዚየም አዘውትራ አትወጣም፡፡ በርካታ እንግዶችም ሉሲን የማግኘት ዕድል አያገኙም፡፡ ለኦባማ የተለየ አቀባበል ማድረጋቸውን ገልጸው፣ ፕሬዚዳንቱ ቅሪተ አካሉን የነኩበትን ምክንያት ያብራሩት ‹‹ልዩ ሰዎች ልዩ ዕድል ያገኛሉ፤›› በማለት ነበር፡፡

በእራት ግብዣው ላይ ‹‹ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ በመሆኗ እናከብራታለን፣ ዕድሜ ጠገቧና መነሻችን የሆነችውን ሉሲም ተዋውቄያታለሁ፤›› ያሉት ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ ‹‹የሰው ዘር መነሻን ስንመለከት ኢትዮጵያውያን፣ አሜሪካውያን እንዲሁም መላው የዓለም ሕዝቦች የአንድ ቤተሰብ ክፍል አንድ ሐረግ እንደሆኑ እንገነዘባለን፤›› ብለዋል፡፡

ቅሪተ አካሉን ለኦባማ ያስጐበኙት ዶ/ር ዘረሰናይ ፖለቲካዊ ቀልድ ጣል ማድረጋቸውንም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ እንደሚሳተፉ ያሳወቁት አሜሪካዊውን ባለሀብት ዶናልድ ትራምፕ በመጥቀስ ‹‹ሁላችንም ሰባት ቢሊዮን ሰዎች፣ ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ከዚህ ሐረግ የተገኘን መሆናችንንም ያሳያል፤›› ብለዋል፡፡

በአሜሪካዊ ተመራማሪ ዶናልድ ጆንሰን በ1967 ዓ.ም. የተገኘችውን ሉሲ መነሻ በማድረግ ፕሬዚዳንቱ በዓለም ላይ ስለሚስተዋለው አለመረጋጋት ተናግረዋል፡፡ ‹‹በዓለም ላይ የሚታየው ግጭት፣ መከራና ሐዘን የሚከሰተው ሰዎች ከአንድ የዘር ሐረግ መገኘታችንን ስለምንዘነጋ ነው፤ ሁላችንም የምንጋራውን አንድነታችንን በማየት ፈንታ ሰው ሠራሽ ልዩነቶቻችን ላይ እናተኩራለን፤›› ብለዋል፡፡  

ከሉሲ ጉብኝት በተጨማሪ ፕሬዚዳንት  ኦባማ  በሌላው ዓለም የማይገኙትና በቤተ መንግሥቱ የሚኖሩትን የኢትዮጵያ አንበሶች አድንቀዋል፡፡

‹‹ምንም እንኳ የውሾቼን ደኅንነት ማረጋገጥ ቢኖርብኝምጠቂቶቹን ወደ ዋይት ኋውስ መውሰድ እንዳለብኝ ከግምት ውስጥ ሳላስገባ አልቀርም፤›› ማለታቸው ታዳሚዎችን አስፈግገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱን አስተያየታቸውን ከሰጡባቸው ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያ በቡና ዘርፍ ያላት ገናና ስም ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆነችባቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉ ገልጸው፣ ከእነዚህ አንዱ የሆነው ቡና በአገራቸው አሜሪካ ያለውን ተወዳጅነት ተናግረዋል፡፡

‹‹አሜሪካውያን ኢትዮጵያውያን ቡናን በማግኘታቸው ምስጋና ያቀርባሉ፤ ቡና በዓለም ላይ ያሉ ሰዎችን ቀን ከሌሊት የሚጠቀሙት ነው፡፡ እኛም ዋይት ሐውስ ውስጥ እንጠቀመዋለን፤›› ብለዋል፡፡

ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የመጀመሪያው በመንበራቸው ላይ ያሉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣ ከኢትዮጵያ አስቀድሞ የአባታቸውን አገር ኬንያ መጐብኘታቸው ይታወሳል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ማክሰኞ (ሐምሌ 21 ቀን 2007 ዓ.ም.) በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ንግግር ካደረጉ በኋላ ወደ አሜሪካ ተመልሰዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...