‹‹የጦር ኃይላችንን ወደ ጦር ሜዳ መላክ አያስፈልገንም፤ ኢትዮጵያውያን ብርቱና ጽኑ ተዋጊዎች ናቸውና፡፡››
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሐምሌ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት፡፡
ለሁለት ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ያሉት ፕሬዚዳንት ኦባማ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋራ ካደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በኋላ ሽብርተኝነትን በመከላከልና በሶማሊያ የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመግታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እየወሰደው ያለውንና የአልሸባብን ሁለት ዋና ጠንካራ ይዞታቸውን ማስለቀቁን ያደነቁ ሲሆን፣ ‹‹አልሸባብን ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም አብረን የምንሠራቸው ቀሪ የቤት ሥራዎች አሉን፤ በቀጣናው ያለንን የማማከር ሥራችን ብቻ ይቀጥላል፤›› ሲሉም ፕሬዚዳንቱ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡