በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች የብሔሩ የዘመን መለወጫ በዓል ‹‹ፊቼ ጫምባላላ››ን እሑድ ሐምሌ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. በጆሐንስበርግ ከተማ አክብረዋል፡፡ ኑሮዋቸውን በደቡብ አፍሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በዓሉ የተከበረው ስለሲዳማ ባህልና የፊቼ ጫምባላላ አከባበር የሚያወሱ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማቅረብና በልዩ ልዩ ባህላዊ ጭፈራዎች ነው፡፡ ፊቼ ጫምባላላ በብሔር ደረጃ በሐዋሳ ከተማ ጉዱማሌ ባህላዊ አደባባይ ሐምሌ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. መከበሩ ይታወሳል፡፡ ፎቶግራዎቹ የሌምቦ ጭፈራን ያሳያሉ፡፡ (በዮሐንስ አልታሞ ጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪካ)