Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ሐምሌ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በአፍሪካ ኅብረት ዲስኩር ባሰሙበት ቅጽበት

ትኩስ ፅሁፎች

ማባሪያ ያጣው አደጋ

ቅዳሜ ሐምሌ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ማለዳ አንድ ሰዓት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ እምቢልታ ሆቴል አጠገብ ለቆሙት ሦስት ላዳ ታክሲዎች ዕለቱ ገዳም አልነበረም፡፡ ከሩፋኤል አካባቢ በተክለማርያም እንጨት መሰንጠቂያ መንገድ ቁልቁለቱን ይሽከረከር የነበረው ኮንቴነር የጫነ ኒሳን ከባድ ተሽከርካሪ በፈጠረው አደጋ የአንዱን ተሽከርካሪ ባለቤትና ሾፌር ሕይወትን ሲቀጥፍ፤ በፎቶዎቹ እንደሚታየው ሦስቱንም ታክሲዎች ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል፡፡ በአካባቢው የነበሩትን የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችንም ገንድሶ ጥሏል፡፡

(ፎቶ በሔኖክ ያሬድ)

************

ኦቦ- አማ

ባራክ ሁሴን ኦባማ፣

የኅብረ – ቀለማት ሸማ፣

የዘመናችን ኮከብ ኦቦአ’ማ፡፡

ኦባማ – የ47 ዓመቱ ጐልማሣ፣

የአፍሮ – አሜሪካው አንበሳ፣

‹‹ለውጥ! ለውጥ!›› እያለ እያገሣ፣

እንዲያቆም የዚህች ዓለም አበሳ፣

አገር ምድሩን ለለውጥ አነሳሳ፡፡

ለለውጡም ሕዝበ – ዓለም አብሮ፣

የቀለም የዘር ድንበር ሰብሮ፣

ተቃቀፈ – በእንባም ተራጨ…

የይቅር መዝሙር ዘምሮ፡፡

የቆዳ ቀለም ጥቁረት ቅላት፣

የዕውቀት – የሥልጣኔ መለያ መስሎት፣

የቆዳ ቀለም የቀለም ቅብ

ብቻ መሆኑ አልታይ ብሎት፣

የቆዳ ቀለም ልክፍት ከታች – ላይ ወጥሮት፣

ነጣ ያለው ሲታበይ

‹‹አይሆንም!›› እያለ ‹‹እንዴት?!››

ዛሬ እጁን ሰጠ የኦቦ – አ’ማ ጠበል አሽሮት፡፡

‹‹እ. . .ል!. . .ል!›› በይ

የኦባማዋ ሚሼል፣

የኋይት ሐውሷ ጉልላት፣

እንኳን ደብ አለሽ አንቺ ውብ ሴት፣

የብሩህ ዓለም ተስፋ የሰላም እናት፣

በርቺ ጊዜውም ሆነ ዓለም ያንቺው ናት፡፡

ሚሼል – አንቺ ውድ ሴት፣

አቻ የሌለሽ እመቤት፣

ለሰላም ዘምሪ እንዲያበቃ ጦርነት፣

‹‹ይቁም!›› በይ በፍጥረታት ዋይታ ጩኸት፣

‹‹ይብቃ!›› በይ ለሞት ደረት መድቃት፣

ዝንተ ዓለም በደም መፎከር

በደም መከርፋት፡፡

ባራክ ሁሴን ኦባማ፣

የኅብረ- ቀለማት ሸማ፣

የዘመናችን የተስፋዎች ማማ፡፡

የአባት – አያትህ ህልም ደረሰ፣

የቀለም – የዕብሪት ድንበር ፈረሰ፣

የእውነት አብዮት በአንተ ነገሠ፡፡

ለካስ እውነት – እውነት ናት፣

የራሷ ራዕይና ጊዜ አላት፣

ሃይማኖት – ዘር – ቀለም አይበልጣት፣

ኦባማ አቦ – አ’ማ እውነትን በአንተ አየናት፣

ሃይማኖት – ዘር – ቀለም አይበልጣት፣

ዓለም – ድሮም – ዛሬም

አንድና – አንድ ናት፡፡

አሰፋ ጉያ

/እ.ኤ.አ ኖቬምበር 6 ቀን 2008 ዓ.ም./

እኩለ ቀን ከፓሪስ ወደ ሮተርዳም በባቡር ጉዞ ላይ

/የኦባማ የድል ውጤት የተገለፀበት ዕለት/

************

‹‹በድህነት ብታልፉም ሁላችሁም እጅግ አስፈላጊ ናችሁ››

የስምንት ዓመቷ ጆአን ዋማይታ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኬንያን በጐበኙበት ወቅት መጀመሪያ የተቀበለቻቸው ታዳጊ ናት፡፡ ፕሬዚዳንቱ ወደ ኬንያ የተጓዙበት ኤርፎርስ ዋን ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ ዓርብ ዕለት ሲያርፍ በጉጉት ይጠባበቁ የነበሩ ሰዎችን ቀልብ መሳብ ችላለች፡፡ ጆአን እቅፍ አበባ ይዛ ነጭ በነጭ ለብሳ ነበር በአየር መንገዱ የተገኘችው፡፡ አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ኦባማ ከአውሮፕላኑ ከወረዱ በኋላ እጃቸውን ለሰላምታ እያውለበለቡ ወደሚጠብቋቸው ባለሥልጣናት ሲያመሩ ታዳጊዋ እቅፍ አበባውን ሰጥታቸዋለች፡፡ ፕሬዚዳንቱም አበባውን ከተቀበሏት በኋላ አቅፈዋት ፎቶግራፍ ተነስተዋል፡፡ ለ30 ሰከንዶች ያህል ከታዳጊዋ አጠገብ ሆነው ነበር፡፡ ጆአን ናይሮቢ በሚገኝ ማይሪከኒ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ስትሆን፣ ለፕሬዚዳንቱ አቀባበል ካደረገች በኋላ ሰኞ ዕለት ወደ ትምህርት ቤቷ ስትመለስ የብዙዎችን ትኩረት ስባ ነበር፡፡ የትምህርት ቤቱ መምህርት የሆኑት ሉሲ አቦንቱ ጆአን ያገኘችውን ትኩረት ተጠቅመው ለተማሪዎቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ‹‹ምንም እንኳን በድህነት ብታልፉም ሁላችሁም እጅግ አስፈላጊ ናችሁ፤›› ብለዋል፡፡ መምህርቷ ጆአን ባገኘችው ከፍተኛ ትኩረት በመጠኑ መደናገሯንም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ታታሪ፣ ሥነ ሥርዓት ያላትና ኃላፊነቷን በአግባቡ የምትወጣ ናት፤›› በማለትም ገልጸዋታል፡፡

 

 

 

 

Fatal error: Allowed memory size of 268435456 bytes exhausted (tried to allocate 72 bytes) in /home/ethiopianreporte/public_html/archive/includes/database/query.inc on line 1804

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች