Saturday, January 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልስለአክሱም ሐውልት ጥገናዊ ሒደት በተዘጋጀው ጥናት ላይ ሊመከር ነው

ስለአክሱም ሐውልት ጥገናዊ ሒደት በተዘጋጀው ጥናት ላይ ሊመከር ነው

ቀን:

የጥንታዊት ኢትዮጵያ መዲና የነበረችው አክሱም፣ ተመራማሪዎች እንደሚገልጿት የኃያል መንግሥት ዋና ከተማ፣ ቀጥሎም የሃይማኖት ማዕከል ብሎም ክርስቲያናዊ መንግሥትን በአፍሪካ ውስጥ መመሥረቷ ሰነዶች ያመለክታሉ፡፡ የኢትዮጵያ ክርስትና መለያ የሆነው ታቦተ ሕግ በመያዝም በርካታ ምዕመናንም በማስተናገድ ትታወቃለች፡፡

 እንደ ባለታሪኩ ፍራንሲስ አንፍሬ የአክሱም መንግሥትና ከተማ በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዓለም ከሚገኙት አራት መንግሥታት ከሮም፣ ከፋርስና ከቻይና ቀጥሎ አራተኛው ኃያል መንግሥት ነበረች፡፡ ለኃያልነቷ ምስክር ግዙፍ ሐውልት፣ ግዙፍ የድንጋይ፣ ጠረጴዛ፣ ግዙፍ የዘውድ መሠረታዊ ድንጋይ የተሰባበሩ ትላልቅ ዐምዶች፣ የነገሥታት መቃብር ከተለያዩ የማይዳሰሱ አፈ ታሪኮችና ባህሎች ጋር ከመገኘታቸውም በላይ ጎብኚን የጥንቱ ታሪክ ምን ያህል ታላቅ እንደነበር ያሳያል፡፡

ታሪካዊቷ አክሱም ከአራት አሠርታት በፊት በዩኔስኮ (የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት) የዓለም ቅርስ ሆና ተመዝግባለች፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ዩኔስኮን ጭምር ያሳሰበ የአክሱም ሐውልቶችን ጨምሮ በቅርሶቿ ላይ አደጋ እየደረሰ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲሰማ ቆይቷል፡፡ በተለይ ነባሩ ሐውልት ከሮም የመጣው ሐውልት ባጠገቡ ሲተከል ጉዳት እንዳያደርስበት ተብሎ በካቦ እንዲታሰር ከተደረገ 10 ዓመት በላይ ማስቆጠሩ ብዙዎችን በተለይም ባለሙያዎችን ማስጋቱ አልቀረም፤ አንድ እንዲባል ማሳሰቢያ ከመስጠትም አልተቆጠቡም፡፡

ጉዳዩን በኃላፊነት እየተከታተለ ያለው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ባለፈው ግንቦት 2009 ዓ.ም. 24 ሜትር ርዝመት ያለውን ሐውልቱን በአንድ ዓመት ውስጥ ለማደስ በአክሱም ከተማ ከሁለት ተቋማት ከአገር በቀሉ ኤምኤች ኢንጂነሪንግና ከጣሊያን የተመለሰውን ሐውልት ዳግም ተከላውን ባከናወነው ስቱዲዮ ክሮቺ በተባለ የጣሊያን አማካሪ ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርሞ ነበር።

በስምምነቱ መሠረት ጥናቱ ባለመጠናቀቁና አማካሪ ድርጅቶቹ ተጨማሪ ጊዜ በመጠየቃቸው ጥገናው በመዘግየቱ እስካሁን እድሳት አለመጀመሩን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ የባለሥልጣኑ የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ዘለቀ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አማካሪ ተቋማቱ ያጠናቀቁት ጥናት ባለፈው ሳምንት ለባለሥልጣኑ አስገብተዋል፡፡ በተዘጋጀው ጥናት ላይ ከዘርፉና ከታሪክ  ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ ምክክር እንደሚደረግ፣ ቴክኒካዊ ግብዓት ይሰበሰባል፡፡ በአክሱም ከተማም ከማኅበረሰቡ ጋር መድረክ ከተዘጋጀ በኋላ ወደ ሥራው እንደሚገባ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

በፋሺስት ጣሊያን ወረራ (1928-1933) ዘመን ተዘርፎ የሄደውና 1999 .ም. ዳግም የተመለሰው ሐውልት ሲተከል ነበር ነባሩ ሐውልት እንዳይነቃነቅና ለአደጋ እንዳይጋለጥ ካቦ እንዲታሰርለት  የተደረገው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14...

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ...

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ...