Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሪል ስቴትና የአከራይ ተከራይ አዋጅ በድጋሚ እንዲስተካከል ታዘዘ

የሪል ስቴትና የአከራይ ተከራይ አዋጅ በድጋሚ እንዲስተካከል ታዘዘ

ቀን:

  • የተስተካከለው ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል

በሪል ስቴት ቤቶች ግብይት፣ በመኖሪያ ቤት አከራይና ተከራይ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩና በኅብረተሰቡ ዘንድ ተጠባቂ የሆኑ ሦስት ረቂቅ አዋጆች በጥቅል ተዘጋጅተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከቀረቡ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሦስቱም ረቂቅ አዋጆች ተነጣጥለው እንዲዘጋጁ በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ሦስቱን ረቂቅ አዋጆች በተናጠል እንዲያዘጋጅ ትዕዛዝ የተሰጠው የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር፣ ሦስቱን አዋጆች በተናጠል አዘጋጅቶ ሰሞኑን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡ ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የሪል ስቴት ግንባታ ከሚያካሂዱ ኩባንያዎች ውስጥ በርካታዎቹ በገቡት ውል መሠረት ለደንበኞቻቸው ቤቱን የማያስረክቡ በመሆኑና ለዓመታት ያላስረከቡ በመኖራቸው፣ እንዲሁም አስረከቡ ከተባለም እጅግ አዘግይተው በውል ላይ የተቀመጡ ጉዳዮችን ጥሰው ስለሆነ የሪል ስቴት ግብይትን አደገኛ አድርጎታል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እነዚህ ምክንያቶች ሻጭና ገዥን ለከፍተኛ ውዝግብ ሲዳረጉ የቆዩ በመሆናቸው፣ መንግሥት የሪል ስቴት ዘርፍ የሚዳኝበትን ሕግ ለማዘጋጀት ተገዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ከፍተኛ ቅሬታ የሚያነሳው በየጊዜው እየናረ በሚገኘው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ላይ ነው፡፡

በተለይ በአዲስ አበባና በክልል ዋና ዋና ከተሞች በየጊዜው ያለምንም በቂ ምክንያት እየጨመረ የሚሄደው የመኖሪያ ቤት ዋጋ ንረት ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠረ በመሆኑ መንግሥት የኬንያ፣ የሲንጋፖርና የመሳሰሉ አገሮች ልምድ ከግንዛቤ ገብቶ ሕግ እንዲዘጋጅ አዟል፡፡ ከዚህ ጋርም የመንግሥት ይዞታዎች የሆኑ ቤቶችም የሚተዳደሩበት ወጥ ሕግ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

እነዚህ ሦስት ረቂቅ አዋጆች በጥቅሉ ተዘጋጅተው ከእነ ማብራርያቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከቀረቡ አምስት ዓመታት ቢቆጠሩም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በድጋሚ ተነጣጥለው እንዲዘጋጁ ወስኗል፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አምባቸው መኰንን (ዶ/ር) ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ አዋጆቹ ተነጣጥለው ሲዘጋጁ የቀሩ ሐሳቦችም በደንብና በመመርያ ተደራጅተዋል፡፡

‹‹በአዋጆቹ ላይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተነጋግሮ እንዲያፀድቀው ተልኳል፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት ዘርፍ ጉልህ ሥፍራ ያለው የፍሊንትስቶን ሆምስ ባለቤት አቶ ፀደቀ ይሁኔ፣ በአንድ የተዘጋጁት ሦስቱ አዋጆች ዘግይተዋል ይላሉ፡፡

አቶ ፀደቀ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሪል ስቴት ግብይትን በተመለከተ የተዘጋጀው አዋጅ የያዛቸው ነጥቦች፣ በአሁኑ ወቅት የሪል ስቴት ቤቶችን የሚገዛ ሰው በቂ መረጃ የያዘ በመሆኑ ተግባራዊ እየሆኑ ነው ማለት ይቻላል፡፡

‹‹የሪል ስቴት ገዢ የሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ንቃት ህሊና እያደገ በመምጣቱ፣ አጭበርባሪውንና በትክክል የሚሠራውን ለይቷል፤›› ሲሉ አቶ ፀደቀ አስረድተዋል፡፡

አቶ ፀደቀ እንደሚሉት ግን የአከራይና ተከራይ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረው ክፍል ባለማወቅ፣ ወይም ሌሎች ሥራዎች ስለበዙ ሳይፀድቅ ዘግይቷል የሚል እምነት የላቸውም፡፡

‹‹የአከራይ ተከራይ አዋጅ መልካም ገጽታዎች አሉት፡፡ አዳዲስ ቤቶችን ገንብተው ለሚያከራዩ አዋጁ ማበረታዎች አሉት፡፡ ከዚህ ውጪ ያሉ አከራዮች ግን በሕጉ ላይ የተቀመጡ አንቀጾች ምቾት አይሰጡዋቸውም፡፡ ከዚህ አንፃር ቤት አከራዮች የባለሥልጣናት ተፅዕኖ ይኖርብናል ብለው በማሰብ ሕጉ እንዳይወጣ ተፅዕኖ አድርገዋል ብዬ አምናለሁ፤›› ብለዋል፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አዋጆቹን በተናጠል አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ የሚያፀድቅበት ጊዜ ግን አሁንም አልታወቀም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...

ወዘተ

ገና! ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤ ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ። በዳዴ ዘመኔም፣ በ'ወፌ ቆመችም!'፤ አውዴ ክፉ ነበር...

የአስፕሪን ታሪክ

በቤት ውስጥ የሚገኝ የመድኃኒት መደርደሪያ፣ ምንም ቢሆን፣ እስፕሪንን ሳይጨመር...