Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመሬት ካዳስተር ምዝገባ በቴክኖሎጂ ውድቀት ምክንያት በዕቅዱ መሄድ አልቻለም

የመሬት ካዳስተር ምዝገባ በቴክኖሎጂ ውድቀት ምክንያት በዕቅዱ መሄድ አልቻለም

ቀን:

የሙስና መፈልፈያ ናቸው ከተባሉ ዘርፎች ግንባር ቀደም የሆነውን መሬት በአግባቡ ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሎ የተጀመረው፣ የካዳስተር ሥራ በአሳሳቢ ደረጃ እየተጓተተ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በፌዴራል፣ በአዲስ አበባ ከተማና በአራቱ ክልሎች ዋና ዋና ከተሞች የመሬት መረጃዎችን የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በካዳስተር መዝግቦ ለመያዝ የተጀመረው ሥራ፣ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ እየተንፏቀቀ ነው ተብሏል፡፡

ረቡዕ የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ‹‹በከተማ ካዳስተር ሥርዓት ግንባታ የኅብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ሚና›› በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ውይይት ተካሂዶ ነበር፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች በውይይቱ በወቅት እንደገለጹት ይህ ሥራ በ2001 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን፣ በኅዳር 2004 ዓ.ም. የወጣው የሊዝ አዋጅ በሦስት ዓመት ውስጥ ምዝገባው እንደሚጠናቀቅ ድንጋጌ አስቀምጦ ነበር፡፡

ነገር ግን እስካሁን የይዞታ ማረጋገጫ የተሠራው ለ122 ሺሕ ይዞታዎች ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ የ70 ሺሕ የሚሆኑት መብት ተፈጥሮላቸዋል፡፡ ምዝገባ የተካሄደባቸው ግን 30 ሺሕ ይዞታዎች ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም መነሻው የካዳስተር ቴክኖሎጂ በአግባቡ መሥራት ባለመቻሉ ሲሆን፣ በአብዛኛው ሥራው እየተከናወነ ያለው በወረቀት ምዝገባ (ማንዋል) በመሆኑ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የሰነድ አልባ ይዞታ መኖር፣ የተነፃፃሪ ካርታ ያላቸው ባለይዞታዎች ዕጣ ፈንታ በአግባቡና በዕቅዱ መሠረት ባለመፈታቱ የሥራ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ሆኗል ተብሏል፡፡

ከአዲስ አበባ ጀምሮ ለሥራው መጓተት ምክንያት ነው ያሉትን ሐሳብ፣ የኦሮሚያ ክልል መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቃሲም ሬጤ ገልጸዋል፡፡

አቶ ቃሲም እንዳሉት፣ ቀደም ሲል የነበረው የመሬት አስተዳደር ችግር ያለበት በመሆኑና ኅብረተሰቡ ለካዳስተር ምዝገባ ያለው አመለካከት የተዛባ ስለሆነ በታሰበው ልክ መሄድ አልተቻለም፡፡

የሚመለከታቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ይህ የካዳስተር ምዝገባ ሥራ ለአገሪቱ አዲስ በመሆኑ ተግዳሮት እንደገጠመው ገልጸዋል፡፡

ከዚህ አንፃር የቴክኖሎጂው አዲስ መሆን፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል አለመኖርና የሰነድ አልባና ሕገወጥ ይዞታዎች መኖር ሥራው በፍጥነት እንዳይካሄድ ማነቆ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እነዚህን ማነቆዎች ለመፍታት ጊዜ የወሰደ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን ችግሮቹ እየተቃለሉ ስለሆነ በ23 ከተሞች የተጀመረው ሥራ ወደ 30 ከተሞች እንዲያድግ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የካዳስተር ምዝገባ ዋናው ጠቀሜታ የመንግሥት፣ የግል፣ የማኅበራትና የመሳሰሉ ይዞታዎችን በተገቢው መንገድ አውቆ ለማደራጀት ነው፡፡ ይህም አሠራር ለይዞታ ባለቤቶች በሕግ ፊት ሁነኛ ዋስትና ይሰጣል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...