Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ንግድ ባንክ ግዙፍ የንግድ ተቋማት የሚገለገሉበትን የኦራክል ሶፍትዌር ገዛ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በመጪው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወይም በአሥር ወራት ውስጥ ይተገበራል የተባለውን ዘመናዊ የኦራክል ኩባንያ ሶፍዌርን በመግዛት ከባንክ አገልግሎት በስተጀርባ ያሉትን ሥራዎቹን ለማዘመን እንደሚያስችለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡

ባንኩ በመጪው ነሐሴ ወር መግቢያ ላይ ያስጀምረዋል የተባለው ሶፍትዌር ‹‹ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ- ኢአርፒ›› የሚባለው ሲሆን በዚህ መሠረትም የሰው ኃይሉን ብቃት፣ ሥልጠናና መሰል ጉዳዮችን ለማስተዳደር፣ የፋይናንስ ማኔጅመነቱንና ቋሚ ሀብቱን ለማስተዳደር፣ ግዥዎችን ለመቆጣጠር፣ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶችን ለማውጣት እንዲሁም የቢዝነስ ኢንተለጀንስ ሥራዎችን የዳታ ቋቶችን ለማስተዳደር ከዚህ በተጨማሪ ባንኩ በእነዚህ መረጃዎች ላይ ተመርኩዞ ከሚያከናውናቸው የንግድ ልውውጦችን በማስመልከት በየጊዜው ሪፖርቶችን ለማመንጨት የሚያስችል ሶፍትዌር እንደሆነ ባንኩ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡

የንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ ባንኩ የኦራክል ምርት የሆነውን ሶፍትዌር በመግዛት በህንዱ ቴክ ማሂንድራ ኩባንያ አማካይነት ለመተግበር ስምምነት ፈጽሟል፡፡ በመሆኑም በነሐሴ ወር መግቢያ ላይ ትግበራው ይጀመራል ለተባለው ሶፍትዌር፣ ለፈቃድ ግዥ 2.6 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለዝርግታው 2.3 ሚሊዮን ዶላር በጠቅላላው 4.9 ሚሊዮን ዶላር ወይም 98 ሚሊዮን ብር ያህል ወጪ አድርጓል ተብሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ በየዓመቱ ለሶፍትዌር ፈቃድ ከከፈለው ውስጥ በየዓመቱ 22 ከመቶ ለፈቃድ ማደሻ ክፍያ እንደሚፈጽም አቶ ኤፍሬም ገልጸዋል፡፡ አዲሱ የንግድ ባንክ ቴክኖሎጂ ከኮር ባንኪንግና ከስዊፍት ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት መስጫ ቴክኖሎጂዎች የተለየ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

 በሁሉም የባንኩ የውስጥ አሠራሮች ውስጥ ከባንክ መደበኛ ሥራ ባሻገር የሚተገበው ይህ ሶፍትዌር የባንኩን ሀብት በውጤማነት ለማስተዳደር ከማስቻል ባሻገር ብቃቱን እንደሚያሻሽለውና በጠቅላላ የባንኩን መሠረታዊ የአሠራር ሥርዓት በመቀየር ረገድ ከትልልቅ ኩባንያዎች ጎራ የሚያሰልፈው ቴክኖሎጂ መሆኑን የገለጹት በኢትዮጵያ የቴክ ማሂንድራ ወኪል ኩባንያ የሆነው የፌርፋክስ ቴክኖሎጂስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማቸው አድማሴ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ግርማቸው ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ ንግድ ባንክ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታል ሥርዓት ውስጥ የሚያስገባውን ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ ቀዳሚ ባንክ ይሆናል፡፡ 

ኦራክል ኩባንያ ከሚያመርታቸው ቴክኖሎጂዎች ውስጥ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከዋሉት መካከል የኮር ባንኪንግ ሶፍትዌር በብዛት ይታወቃል፡፡ የህንዱ ማሂንድራ ግሩፕ ኩባንያ አካል የሆነው ቴክ ማሂንድራ አዲሱን የንግድ ባንክ ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ በመተግበር የሚሠራ ተቋም ነው፡፡ በ51 አገሮች ውስጥ ከ767 በላይ ደንበኞችን ያፈራ ጠቅላላ ሀብቱም ከ3.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው፡፡ ማሂንድራ ግሩፕ በበኩሉ 16.9 ቢሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅስ ተቋም ነው፡፡

ከተቋቋመ 73 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ፣ አንድ ሺሕ ቅርንጫፎችን በመላው ኢትዮጵያ በመክፈት የደንበኞቹን ቁጥር ወደ አሥር ሚሊዮን ያደረሰ ግዙፍ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም ለመሆን በቅቷል፡፡ ጠቅላላ ሀብቱም 276.3 ቢሊዮን ብር ወይም ከ14 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚገመት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች