Sunday, January 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአከራይ ተከራይና የሪል ስቴት ግብይት አዋጅ እስካሁን አለመፅደቁ ጥያቄ አስነሳ

የአከራይ ተከራይና የሪል ስቴት ግብይት አዋጅ እስካሁን አለመፅደቁ ጥያቄ አስነሳ

ቀን:

በአከራይ ተከራይና በሪል ስቴት ያለውን የተዘበራረቀ ግብይት ሥርዓት ለማስያዝ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ እስካሁን ፀድቀው ወደ ተግባር ባለመሸጋገሩ፣ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጥያቄ እያነሱ ነው፡፡

የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በተናጠል ያዘጋጃቸው የአከራይ ተከራይ ግብይት፣ የሪል ስቴት ልማትና ግብይት፣ የመንግሥት ቤቶች አስተዳደርን በሚመለከት ያዘጋጃቸውን ሦስት አዋጆች በአንድ አዋጅ አጠቃሎ ረቂቁን አቅርቧል፡፡

በዚህ አዋጅ ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር የመጨረሻ አስተያየት ከሰጠ በኋላ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ተልኮ ይፀድቃል ቢባልም፣ አዋጁ የውኃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል በማለት የአዋጁን መፅደቅ የሚጠባበቁ ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ፍትሕ ሚኒስቴር በአዋጁ ላይ አስተያየት ሰጥቶ ከላከ ወራት ቢቆጠሩም፣ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አዋጁን ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት አለመላኩ ታውቋል፡፡

አዋጁ በፍጥነት ተግባር ላይ ቢውል በርካታ ጥቅሞችን ያስገኛል በማለት የሚናገሩት ቅሬታ አቅራቢ ነዋሪዎች፣ በተናጠል የተዘጋጁት ረቂቅ አዋጆች ከሁለት ዓመታት በላይ ማስቆጠራቸው አግባብ አይደለም ይላሉ፡፡

ሦስቱ ረቂቅ አዋጆቹ በአንድ አዋጅ ሥር ከተጠቃለሉ በኋላ በፍጥነት ይፀድቃሉ በማለት ቢጠብቁም፣ አዋጁ ሊፀድቅ ባለመቻሉ ለጉዳት ተዳርገናል ይላሉ ነዋሪዎች፡፡ በከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ባለቤትነት የአከራይ ተከራይ ሕግ ተዘጋጅቷል፡፡ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአሁኑ ወቅት እየናረ የመጣውን የመኖርያ ቤት ኪራይ ውድነት ሥርዓት ለማስያዝ የሌሎች አገሮች ልምድ የተካተተበት አሠራር መፈጠር ያስፈልጋል ተብሎ አዲስ ሕግ ተዘጋጅቷል፡፡

በዚህ ሕግ መሠረት እንደ መኖሪያ ቤቱ ሁኔታና መኖሪያ ቤቱ እንደሚያሟላው ምቹነት የግብይት ዋጋና ደረጃ ተዘጋጅቷል፡፡ የዋጋ ደረጃው የግል አከራይ ባለይዞታዎችንም እንደሚያካትት በሚኒስቴሩ የመኖሪያ ቤቶች ልማትና የመንግሥት ቢሮ ከወራት በፊት ከንግድ ሚኒስቴር ጋር ሆኖ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጾ ነበር፡፡ ይህ አዋጅ መዘጋጀቱንና በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ይፀድቃል በማለት ሲጠባበቁ የነበሩ ነዋሪዎች፣ አዋጁ ባለመፅደቁ ቅሬታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ያዘጋጀው የሪል ስቴት ልማትና ግብይት አዋጅ ሲካሄድ የቆየው የሪል ስቴት ልማት በተዘበራረቀና ወጥነት በጎደለው መንገድ በመሆኑ፣ የሪል ስቴት ደንበኞች መብት ለማስጠበቅና በዘርፉ የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈቱበት አሠራር ባለመኖሩ አዋጅን ማውጣት ማስፈለጉን ይገልጻል፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት በሪል ስቴት አልሚዎችና በገዢዎች መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ሲከሰት የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንን የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት አዋጅ ማውጣት ያስፈልገል በማለት ሚኒስቴሩ በ2003 ዓ.ም. ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቷል፡፡

ነገር ግን በአዋጁ ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር የመጨረሻ አስተያየት ሰጥቶበት ለከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ቢልክም፣ ሚኒስቴሩ አዋጁን ወደሚያፀድቀው ክፍል አለመላኩን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚኒስቴሩ ኃላፊዎች አስተያየት እንዲሰጡ በተደጋጋሚ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...