‹‹ለተሳትፏችሁ ወሰኑ ሰማይ ነው››
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የኦሮሚያ ክልል ዳያስፖራ ሳምንት መከበር አስመልክቶ ሐምሌ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የተናገሩት፡፡
‹‹የዳያስፖራ የነቃ ተሳትፎ ለሕዳሴያችን›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ባለው የኦሮሚያ ዳያስፖራዎች ሳምንት፣ ዳያስፖራዎች ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ልምዳቸውንም በመጠቀም በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት የበኩላቸውን ሚና ከመጫወት ባለፈ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሆነ በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ዕውቀትና ክህሎት ለትውልድ ማካፈል እንደሚጠበቅባቸው ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዚህም ዳያስፖራው በአገሩ ልማት የመሳተፍ ሒደትም እስከ ሰማይ ጥግ ድረስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሐምሌ 26 ቀን የተጀመረው የኦሮሚያ ዳያስፖራዎች ሳምንት ነሐሴ 4 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ፣ በብሔራዊ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ቀን ከነሐሴ 6 ቀን እስክ ነሐሴ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ‹‹ሁሉም ለሕዳሴ›› በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡