Friday, June 9, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዓረብ ባንክ ለኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ብድር ለመስጠት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የዓረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ተብሎ የሚጠራው የፋይናንስ ተቋም፣ በአፍሪካ መገኛውን በማድረግ መንግሥታት ለሚያካሂዷቸው የልማት ሥራዎች ብድር በመስጠት ይታወቃል፡፡ ይህንን አካሄዱን በማሻሻል የግሉ ዘርፍ የባንኩን ፋይናንስ የሚያገኝበትን መንገድ መቀየሱን የባንኩ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሲዲ ውድ ታብ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ምን ያህል ገንዘብ ለማደበር መዘጋጀቱ ይፋ አልተደረገም፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳስታወቁት፣ ከዚህ ቀደም ለአፍሪካ መንግሥታት በኢኮኖሚና ማኅበራዊ መስኮች ለሚያከናውናቸው የመሠረተ ልማትና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ብድር ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያ የባንኩን ፋይናንስ ሲያገኙ ከነበሩ 32 አገሮች መካከል ትመደባለች፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ባንኩ በአፍሪካ አገሮችና በዓረቡ ዓለም መካከል የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ለተሰማሩ ትልልቅ፣ መካከለኛና አነስተኛ ኩባንያዎች ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከዚህም ባሻገር ባንኩ የአዋጭነት ጥናቶችን ለሚፈልጉ፣ የገበያ ጥናት፣ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ሥራዎችን ለሚፈልጉና ሌሎች ጥናቶችና የባለሙያ ትንታኔዎችን ለሚፈልጉም የቴክኒክ ድጋፎችን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ የሚገኙ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ከባንኩ ተጠቃሚ ለመሆን በቀጥታም ሆነ በአገር ውስጥ ንግድ ባንኮች በኩል ከባንኩ የፋይናንስ አቅርቦት ለማግኘት የሚችሉባቸውን አሠራሮች ይዞ ብቅ ማለቱን ጠቁመዋል፡፡

ለአፍሪካ መንግሥታት የረጅም ጊዜ ብድርና ከአነስተኛ ወለድ ጋር ብድር ሲሰጥ የቆየውን ዓረብ ባንክ፣ ለንግድ ማኅበረሰቡ ግን በንግድ አግባብ ላይ የተመሠረተ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን የገለጹት ዶክተር ታብ፣ ባንካቸው በኢትዮጵያ መንግሥት የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በተለይ በንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ ባንኮች ብድር ለማቅረብ ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል፡፡ በወጪና ገቢ ንግድ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ፣ ከኢትዮጵያ ወደ ዓረብ አገሮች ምርቶቻቸውን የሚልኩና በተመሳሳይ ከዓረቡ ዓለም ምርቶችን የሚያገቡ ኩባንያዎች  ምን ያህል ገንዘብ ሊያበድር እንደሚችል ተጠይቀው፣ ይህንን የሚወስነው የግሉ ዘርፍ የመበደር ፍላጎት እንደሆነ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ የተመሠረተው የዓረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ዕድገት፣ ከአፍሪካ አገሮች መካከል የባንኩን ፋይናንስ ለማግኘት 44 በአገሮች ብቁ እንደሆኑ ቢያስታውቅም ከ32 ያልበለጡ አገሮች ብቻ እስካሁን የባንኩን ብድር በማግኘት ላይ ይገኛሉ፡፡ ባንኩ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው የመንግሥት ፕሮጀክቶች ውስጥ የኤርፖርቶች ግንባታ፣ የውኃ ሥራዎች፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች፣ የግብርና መስኮች፣ ጤናና ትምህርት በባንኩ ፋይናንስ የሚደረጉ በአፍሪካ መንግሥታት የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች ናቸው፡፡

በግሉ ዘርፍ ከሚከናወኑት መካከል በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ የዓረብ አገሮች ኩባንያዎችና በዓረቡ ዓለም ኢንቨስት ያደረጉ የአፍሪካ ኩባንያዎች ማበረታቻ ከባንኩ የሚያገኙባቸው አሠራሮች እንዳሉት፣ በወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩትን ኩባንያዎች ፋይናንስ ከማድረግ በዘለለም በአነስተኛና መካከለኛ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ኩባንያዎችን ፋይናንስ ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ዶክተር ታብ አስታውሰዋል፡፡

የዓረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት እንደ ኩዌት ልማት ፈንድ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ልማት ፈንድ፣ አቡዳቢ ልማት ፈንድ፣ የነዳጅ ላኪ አገሮች ድርጅት (ኦፔክ) ፈንድና ከሌሎች የዓረቡ ዓለም የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመሆን የሚሠራ ተቋም ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች