Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ባልትናዶሮ በቺዝና በሞርቶዴላ

  ዶሮ በቺዝና በሞርቶዴላ

  ቀን:

  ጥሬ ዕቃዎች

  4 የዶሮ መላላጫ

  4 የሾርባ ማንኪያ ቤት የተሠራ ቺዝ

  4 ስላይስ ሞርቶዴላ

  6 የሾርባ ማንኪያ ክሬም

  2 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ

  ዘይት

  ጨውና ቁንዶበርበሬ

  አዘገጃጀት

  • በቅድሚያ ኦቨኑን በ350 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ማሞቅ፣
  • ዶሮውን በደንብ ማጠብ፣
  • ዶሮውን መሀል ለመሀል በቢላ መሰንጠቅ፣
  • ቤት የተሠራውን ቺዝ በጨውና በቁንዶበርበሬ መቀመም፣
  • ሞርቶዴላውን በትናንሽና በደቃቁ መክተፍ፣
  • ከትፎ ወደቺዙ ጨምሮ መደበላለቅ፣
  • በማንኪያ እየጨለፉ ቺዙንና ሞርቶዴላውን ወደ ተቀደደው ዶሮ ውስጥ መጠቅጠቅ፣
  • ጠቅጥቆ በጥርስ እንጨት ማሸግ (ሲጠበስ ቺዙ እንዳይወጣ)፣
  • በመጥበሻ ዘይት አግሎ ዶሮውን ጨምሮ በሁሉም በኩል እያገለባበጡ መጥበስ፣
  • ከመጥበሻው አውጥቶ ወደ መጋገሪያ ትሪ አድርጐ ኦቨን ውስጥ ለ40 ደቂቃ ማብሰል፣
  • ዶሮ በተጠበሰበት መጥበሻ የገበታ ቅቤና ክሬም ጨምሮ ማማሰል፣
  • ዶሮውን ከበሰለ በኋላ ከኦቨን ውስጥ ማውጣት፣
  • ሲቀርብ ክሬሙን ፈሰስ አድርጐ ማቅረብ፡፡
  • ጆርዳና ኩሽና ‹‹የምግብ አዘገጃጀት›› (2007)
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img