Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ሥነ ፍጥረትሐዘንተኛ ዋኔ

ሐዘንተኛ ዋኔ

ቀን:

ሐዘንተኛ ዋኔ (African Mourning Dove-Streptopelia decipiens) አመዳማ መልክ ያላቸው መጠነኛ ዋኔዎች፡፡ አብዛኛው አካላቸው አመዳማ ሲመስል ከታች አካላቸው ሐምራዊ ቅብ አለው፡፡ ዓይናቸው ገርጣ ያለ ነው፡፡ አንገታቸው ከኋላ ሰፋ ያለ ጥቁር እሪፊ ሲኖረው፣ የክንፋቸውና የጅራታቸው ዳርቻ እንደዚሁ ጥቁር ቀለም አለው፡፡ በውኃ ዙሪያ የሚገኙ የግራር ዛፎችን ያዘወትራሉ፡፡

****

አንገተ ፍንጥቅ ዋኔ

- Advertisement -

አንገተ ፍንጥቅ ዋኔ (Laughing Dove –Streptopelia senegalensis) ቀላ ያለ ቀለም ያላቸው ትናንሽ ዋኔዎች፡፡ ክንፋቸው ግራጫ-ሰማያዊ ቀለም ያለው ሲሆን፣ ሆዳቸውና ጅራታቸው በዋነኛነት ነጭ ነው፡፡ ዓይናቸው ጥቁር ቡናማ ቀልም አለው፡፡ አንገታቸውና ደረታቸው ሐምራዊ ሆኖ ጥቁር ነጠብጣብ ከፊለፊት አንገታቸው ይታያል፡፡

በብዙ የኢትዮጵያ አካባቢ የሚገኙና ግራርማና እሾክማ ቁጥቋጦዎችን፣ እንዲሁም እርሻዎችንና የጓሮ ተክሎችን የሚያዘወትሩ ዋኔዎች ናቸው፡፡

  • ከበደ ታደሰ ‹‹የኢትዮጵያ መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ወፎች የኪስ መጽሐፍ›› (2000)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...