Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

ለሥራ ከአዲስ አበባ ወጣ ባልኩ ቁጥር በርካታ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ የገጠር ሰዎችን እመለከታለሁ። ሁልጊዜም ቢሆን የሚገርመኝ ባዶ እግራቸውን መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንዶቹ እንዲያውም ጫማቸውን በዘንግ አንጠልጥለው የሚሄዱ መሆናቸው ነው። ሜዳ ሜዳውን ዘንጠው የተጫሙትን ጫማ ስለታም ድንጋይ ያለው ኮሮኮንች ቦታ ላይ ሲደርሱ ጫማቸው እንዳይጎዳ በማሰብ አውልቀው በእጃቸው ይይዙታል። ቀልድ አይደለም ይኼ እውነት ነው።

በርካታ የጫማ ዓይነቶች በአገራችን ቢኖሩም፣ አብዛኛው የገጠር ሰው የሚጫማው እኛ ‹በረባሶ› ወይም ‹ሞጋ› ብለን የምንጠራው ከጎማ የተሠራ ርካሽ ጫማ ነው። ቦታ መጥቀስ ባያስፈልግም በአንድ አንድ የአገራችን ክፍሎች ይህን ርካሽ ጫማ እንኳን የሚያደርጉ ሰዎች አይገኙም። የአንዳንዱ እግርማ የጫማ ያህል ደርቆ ተሰነጣጥቆ በድን ሆኗል። እንዲህ ያሉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በሥራ ጠንካራ ሰው የሚባሉ እንደሆኑ ይገባኛል። ምናልባትም ባዶ እግር ምቾት ይሰጣቸው ይሆናል። ነገር ግን በጣም ያሳዝናሉ። መካሪ፣ ተቆጪና ተቆርቋሪ አጥተው እንጂ ይኼስ የሚበረታታ አይደለም።

ባዶ እግራቸውን ለስለት የሚሄዱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። የበቁ በየገዳማት ያሉ አባቶችም እንዱሁ። ወይም እንደ ጃማይካዊው የሬጌ ሙዚቀኛው ራስ ኩንተሰብ ‹‹ኢትዮጵያ የተባረከች የተቀደሰች አገር ናት በጫማ አልረግጣትም›› የሚል ዓይነት ሰው ጫማን ሊፀየፍ ይችላል። እነዚህ ሊያሳምኑኝ ይችላሉ። በተረፈ ግን ጫማን በትከሻ አዝሎ በባዶ እግሩ ማዝገም የመረጠን ሰው ምን ሊባል እንደሚችል እንጃ።

ስለ ዳግማዊ አፄ ምንሊክ በጫማ ጉዳይ ያስታወስኩትን ታሪካቸውን ከመጽሐፍ ስላገኘሁት እሱን ጋብዣችሁና ልሰናበት። ታዲያ ጽሑፉን አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጆችዎ ሼር አድርገው በማጋራት አሁንም መጫማት የሚገባቸውን ሰዋች ይመክሩ ወይም ይቆጡ ዘንድ የሚመለከታቸው ሰዎች እንዲረዱ ያድርጉ። (ከአጤ ምኒልክ መጽሐፍ ገጽ 338 በጳውሎስ ኞኞ)

ሰንደል ጫማ እንጂ ሽፍን ጫማ ማድረግ በአገራችን አልተለመደም ነበር። ሽፍን ጫማ የሚጠላበትም ምክንያት የአገራችን የበቅሎም ሆነ የፈረስ እርካብ ጫማውን የማያስገባ ጠባብ ስለነበረ ነው።

አንዳንድ መኳንንት በእግር በሚሄዱበት ጊዜ ነጠላ ጫማ አድርገው ይጓዙና በቅሎ ወይም ፈረስ በሚቀመጡበት ጊዜ ጫማው ወልቆ አሽከር ይይዝና በባዶ እግራቸው ከበቅሎው ይወጡ ነበር። ይህም ሁኔታ እስከኋለኛ ዘመን ድረስ ነበር። እኔም ደርሼበታለሁ (ይላል ጸሐፊው ጳውሎስ)፡፡

ዳግማዊ አፄ ምንሊክ የሽፍን ጫማን ጠቃሚነት ከፈረንጆች ከተረዱ በኋላ ሰፊ እርካብ አሠርተው ሽፍን ጫማ ማድረግ ጀመሩ። መረብ ዊልዴና ሮሰን እንደጻፉት ምንሊክ መኳንንቱ ሁሉ ሽፍን ጫማ እንዲያደርግ ቢመክሩም ሰሚ አጡ። ሽፍን ጫማ የሚያደርግም እንደ ‹ቆማጣ› ተቆጠረ። ምንሊክም ‹ቆማጣ› ያለመሆናቸውን በአደባባይ ባዶ እግራቸውን እያሳዩ ሽፍን ጫማ ቢያደርጉም ተከታይ ጠፋ።

ምንሊክ በውዴታ እንጂ በግዴታ የማያምኑ ሰው ስለነበሩ የልጅ ልጃቸው እያሱን እንኳን ሽፍን ጫማ ማስደረግ አቃታቸው።

ምንሊክ ከአማካሪዎቻቸው ፈረንጆች ጋር ከተማከሩ በኋላ በ1902 ዓ.ም. ከፊት ጣትን፣ ከኋላ ተረከዝን የሚሸፍን ግማሽ ሽፍን ጫማ አሠርተው ‹‹ቆማጣ ላለመሆንህ ግማሽ እግርህ ይታያልና እኔን የወደድክ እኔን ምሰል። ሽፍን መጫሚያ ከእሾህ፣ ከብርድና ከእንቅፋት ከሌላ ነገርም ይከላከልልሃል ብዬ ነውና ለጤናህ ስትል አድርግ፤›› ብለው ችሎት ላይ ከተናገሩ በኋላ ጥቂት ሠራዊት እየቀፈፈው ያን ጫማ ያደርግ ጀመር (ይላይ ጽሑፉ)፡፡

እንዲህ ዓይነት ለእግር ጭምር የሚጨነቁ መሪ ነበሩ እምዬ!! ዛሬም ከመቶ ዓመታት በኋላም ጫማ እንቢ ያሉ ሰዎች አሁንም አሉ። ጫማ መግዣም ያጡ ሰዎች አሉ። በእምዬ ሞት ‹‹ጫማ ከእሾህ፣ ከብርድና ከእንቅፋት ይከላከላልና… ለጤናህ ስትል አድርግ፤›› እርስዎስ የሚያስታውሱት ጫማ አልባ ሰው ይኖር ይሆን?

(ያሬድ ሹመቴ በፌስቡክ ድረ ገጹ ካሰፈረው)

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...