Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕውቅና የሰጠው የቤቶች ልማት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕውቅና የሰጠው የቤቶች ልማት

ቀን:

ኢትዮጵያ በተቀናጀ የመኖሪያ ቤቶች ልማት ለውጥ አምጥታለች ያለው የተባበሩት መንግሥታት ደርጅት (ተመድ) የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጉዳዮች ተቋም ዕውቅና ሰጠ፡፡ ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽት የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ፣ የዕውቅናውን ሠርተፊኬት ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ሰጥተዋል፡፡ አቶ መኩሪያ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የቤቶች ልማት መርሐ ግብር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመጠለያ ችግር ከመቅረፍ በተጨማሪ በሒደቱ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ ‹‹ከ60 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ ከ2,600 በላይ ተቋራጮችና አማካሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር ተፈጥሯል፤›› በማለት አቶ መኩሪያ የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክቱ ያስገኘውን ጠቀሜታ ገልጸው፣ ‹‹በፕሮግራሙ እስካሁን ድረስ ከ136 ሺሕ በላይ ቤቶች ለዕድለኞችና ለልማት ተነሺዎች ተላልፈዋል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ጉዳዮች ተቋም አዳዲስና ፋና ወጊ አስተሳሰቦችን በማመንጨት፣ የዜጎችን ሕይወት ለመለወጥ የቻሉ አካላትን በየዓመቱ ዕውቅና ይሰጣል፡፡ በዚህ መሠረት በዚህ ዓመት በኮሎምቢያ ሜድስን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የ‹‹ፐብሊክ ሰርቪስ አዋርድ›› ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገሮች ከኬንያ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ አግኝታለች፡፡ ለዕውቅና የሚያበቃው መሥፈርት መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ማሻሻል፣ አሳታፊ የፖሊሲ ዝግጅትና የውሳኔ ሰጪነት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንግሥት አሠራርና ሥርዓተ ፆታን ያካተተ መንግሥታዊ አገልግሎት ማቅረብ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም በማቅረብ የተወዳዳረች ሲሆን፣ አወዳዳሪው ተቋም በራሱ መሥፈርቶች ኢትዮጵያን ከገመገመ በኋላ አሸናፊ መሆኗን  አብስሯል፡፡ እ.ኤ.አ. ከሰኔ 23 ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሜድስን ከተማ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ኢትዮጵያ ዕውቅናውን የተቀበለች ሲሆን፣ ባለፈው ሐሙስም በአዲስ አበባ ሒልተን በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለተገኘው ውጤት ጽዋቸውን አንስተዋል፡፡ (ዘገባ በውድነህ ዘነበ፣ ፎቶግራፍ በዳንኤል ጌታቸው)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...