Monday, March 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት የማረሚያ ቤት ኃላፊ ቀርበው እንዲያስረዱ...

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት የማረሚያ ቤት ኃላፊ ቀርበው እንዲያስረዱ ታዘዘ

ቀን:

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው እነ ዘመነ ካሴ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸውና ለሦስት ጊዜያት የተጠሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ባለመቅረባቸው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኃላፊ ያልቀረቡበትን ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱና ምስክሩንም እንዲያቀርቡ ሌላ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸውን የእነ ዘመነ ካሴን ክስ እየመረመረ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ለሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. አቶ አንዳርጋቸውን መቅረብ አለመቅረባቸውን በችሎት ሲያረጋግጥ ግለሰቡ አልቀረቡም፡፡ ለምን እንዳልቀረቡ የማረሚያ ቤት ተወካይ ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤቱ ቢጠይቅም ማንም ምላሽ ሊሰጠው አልቻለም፡፡

ፍርድ ቤቱ ሌላ ትዕዛዝ ሊሰጥ ሲል ከተከሳሾቹ አንዱ ተነስተው ማረሚያ ቤቱ የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፣ አቶ አንዳርጋቸውን የያዛቸው የፀረ ሽብር የጋራ ግብረ ኃይሉ በመሆኑ ማረሚያ ቤቱ የማያቀርብ ከሆነ ለእሱ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ተከሳሹ በመቀጠልም፣ ‹‹ተከሳሹ ፍርደኛ ነው፡፡ ፍርደኛ ደግሞ የሚኖረው ማረሚያ ቤት ነው፡፡ ለምን ማረሚያ ቤቱ እንዲያቀርብ ጥብቅ ትዕዛዝ አይሰጠውም?›› በማለት ጠይቀዋል፡፡ ከታሰሩ ሦስት ዓመታት እንደሞላቸው በመግለጽ ቤተሰቦቻቸው ‹‹የአሸባሪ ቤተሰብ›› እየተባሉ የሚያከራያቸው በማጣታቸው፣ በየቦታው ተበትነው እየተሰቃዩ መሆኑን በመናገር ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው በአጭር ቀጠሮ ቀርበው እንዲመሰክሩላቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ብዛት ያላቸው ምስክሮችን እንደሚሰማና በአጭር ቀናት ማቅረብ እንደማይችል ገልጾ፣ ለጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመኪና ሆነው አገሪቱ በልማት እያደረገች ያለውን ግስጋሴ እየጎበኙ መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በቅርቡ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...