Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየካሳ አዋጁን ለማሻሻል የተዘጋጀ ረቂቅ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ

የካሳ አዋጁን ለማሻሻል የተዘጋጀ ረቂቅ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ

ቀን:

ከከተሞችና ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚፈናቀሉ ዜጎች በድጋሚ የሚቋቋሙበትና የሚካሱበት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ከእነ ድንጋጌው ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተነጋገረበት በኋላ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር አካላት በሰፊው ይመክሩበታል ተብሏል፡፡

የስትራቴጂውና የሕግ ማዕቀፎቹ ባለቤት የፌዴራል የተቀናጀ መሠረተ ልማት ኤጀንሲ ሲሆን፣ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ዋነኛ ባለድርሻዎች ናቸው፡፡

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ለንብረት ካሳ የሚከፈልበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 455/1997 እና ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣው ደንብ ቁጥር 135/1999 በድጋሚ እንዲሻሻል ተወስኗል፡፡

እነዚህ ሕግጋቶች እንዲሻሻሉ የተወሰነው ለልማት ሲባል ከመሀል ከተማ፣ እንዲሁም አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በየጊዜው ሲፈናቀሉ ከወቅቱ ገበያ አንፃር በቂ ካሳ አለማግኘታቸው፣ በቂ ተለዋጭ ቦታ አለማግኘታቸው፣ እንዲሁም የተሻለ ኑሮ ሊኖሩ የሚችሉበት የማቋቋሚያ ስትራቴጂ ባለመቀየሱ ለከፋ ችግር በመዳረጋቸው ነው ተብሏል፡፡  

የፌዴራል የተቀናጀ መሠረተ ልማት ኤጀንሲ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ፈቃድና ሕግ ማስከበር ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ገብረ መድኅን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ስትራቴጂውና የሕግ ማዕቀፎቹ ተዘጋጅተው በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አማካይነት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

‹‹ስትራቴጂው ፀድቆ ተግባራዊ በሚሆንበት ጊዜ ዜጎች የተሻለ ጥቅም ያገኛሉ፤›› ሲሉ አቶ ሰለሞን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተካሄዱ በሚገኙ መጠነ ሰፊ ግንባታዎች በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ በመኖርያ ቤቶች፣ በባቡር መስመሮች፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫና በመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በርካታ ዜጎች ተፈናቅለዋል፡፡

ለልማት ሲባል ከነባር ይዞታቸው የሚነሱ ዜጎች መነሳታቸውን ባይቃወሙም፣ በቂ ካሳ እየተሰጣቸው ባለመሆኑ ባገኙት መድረክ ቅሬታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

በተዘጋጀው ረቂቅ የሕግ ማሻሻያ በተለይ የካሳ ቀመሩ መልካም ሆኖ መዘጋጀቱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ከከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ይህ ስትራቴጂና የሕግ ማዕቀፍ በተግባር እስኪውል ድረስ መንግሥት ዜጎችን ከማፈናቀል ተቆጥቧል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ