Sunday, December 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየዳያስፖራ ቢዝነስ ፎረም አምባሳደር ግርማ ብሩን ሊሸልም መሆኑ ተሰማ

የዳያስፖራ ቢዝነስ ፎረም አምባሳደር ግርማ ብሩን ሊሸልም መሆኑ ተሰማ

ቀን:

–  የዓመቱ የዳያስፖራውያን ተሸላሚዎች ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ ይካሄዳል

በአሜሪካ የሚገኙ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት የመሠረቱትና ላለፉት አሥር ዓመታት ሲንቀሳቀስ የቆየው የዳያስፖራ ቢዝነስ ፎረም፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ በሚካሄደው ዓመታዊ የሽልማት ሥነ ሥርዓት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ብሩን እንደሚሸልም ተሰማ፡፡

ሐሙስ ነሐሴ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ምሽት በሸራተን አዲስ የሚከናወነው ሥነ ሥርዓት፣ ከዳያስፖራው ሳምንት ጋር አብሮ እንዲካሄድ ታስቦ በአዲስ አበባ ሲከናወን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ‹‹የዓመቱ የቢዝነስ ሻምፒዮና›› ተብለው የሚሸለሙት አምባሳደር ግርማ ብሩ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአሜሪካ የዳያስፖራ ቢዝነስ ፎረም ዋና አስፈጻሚ አቶ ዮሐንስ አሰፋ ስለሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ፣ በኢትዮጵያ ልዩ ውጤት ስላስገኙ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ኢንቨስተሮች ከመግለጽ ውጪ ስለ አቶ ግርማ ዕጩነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡ የሚሸለሙት ዲፕሎማት ሽልማቱን ስለመቀበላቸው ማረጋገጫ ባለመስጠታቸው ማን እንደሆኑ ከመግለጽ መቆጠብን እንደሚመርጡ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም የሪፖርተር ምንጮች ተሸላሚው አቶ ግርማ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ እንደ ምንጮች ማብራሪያ ከሆነ አቶ ግርማ የተመረጡት፣ ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ በሚሰጡት ድጋፍና ችግሮች ሲከሰቱም ለመፍታት በሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር ዘንድሮ የልዩ አስተዋጽኦ ተሸላሚ እንደሚሆኑ ይፋ የተደረጉት በኢትዮጵያ የሕምክና አገልግሎት ዘርፍ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሁለት ባለሀብቶች ናቸው፡፡ ከቢዝነስ ፎረሙ በተገኘው መረጃ መሠረት በአሜሪካ ሲማሩና ሲሠሩ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት በማድረግ ትልልቅ የሕክምና ተቋማትን የሚያንቀሳቅሱት አቶ ታምራት በቀለና ዶ/ር አከዛ ጣዕመ ናቸው፡፡

 አቶ ታምራት የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ እህት ኩባንያ ለሆነው ሜድፋርም ሆልዲንግስ አፍሪካ መሥራችና ዋና ሥራ አስፋጻሚ ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2004 ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የላቦራቶሪውን ተቋም በአዲስ አበባ መሥርተዋል፡፡ በአፍሪካ ዓለም አቀፍ መስፈርቶች የጤና ክብካቤ ዕውቅና በማግኘት የሚሠራ ተቋም ለመሆን የበቃ ላቦራቶሪ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ብቸኛው ፈቃድ ያገኘ ተቋም በመሆን የሚንቀሳቀሰው ይህ ላቦራቶሪ፣ ባለፉት አሥራ አንድ ዓመታት ውስጥ 900 ሺሕ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉም የኩባንያው ዝክረ ታሪክ ይዘረዝራል፡፡ ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ታምራት ኑሯቸው በአዲስ አበባ ካደረጉ ሰንብተዋል፡፡

ዶ/ር አከዛ የቅዱስ ያሬድ ጠቅላላ ሆስፒታልንና በቅርቡም አሜሪካን ሜዲካል ሴንተርን ከሸሪኮቻቸው ጋር በመመሥረት በሜዲካል ዳይሬክተርነት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ባሻገርም በግል ሆስፒታሎች ማኅበር ፕሬዚዳንትነት ማገልገላቸውም ይታወቃል፡፡ የሦስት ልጆች አባት የሆኑት ዶክተር አከዛና አጋሮቻቸው የመሠረቷቸው የሕክምና ተቋማት፣ በአዲስ አበባና በአጎራባች አካባቢዎች ለሚኖሩ አንድ መቶ ሺሕ ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም ግማሽ ቢሊዮን ብር በሚጠጋ ካፒታል የሜዲካል ቱሪዝም ይፈጥራል ያሉትን ዘመናዊ ሆስፒታል ለመገንባት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት አቶ አዲስ ዓለማየሁና አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በአሜሪካ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

ዘንድሮ ለአሥረኛ ጊዜ በሚካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ላለፉት ዓመታት በነበራቸው አስተዋጽኦና ድጋፍ የኧርነስት ኤንድ ያንግ ማኔጂንግ ፓርትነትር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ፣ የ251 ኮሙዩኒኬሽንስ ዋና ዳይሬክተርና ባለቤት አቶ አዲስ ዓለማየሁን ጨምሮ አምስት ግለሰቦችም ተሸላሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

አቶ ዮሐንስ ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፣ ምንም እንኳ የዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን ቢዝነስ ፎረም ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚ ጎራ የማይወግንና ከፖለቲካ ነፃ ተቋም ቢሆንም፣ በውጭና በአገር ውስጥ ፍረጃዎች እየደረሱበት ይገኛል፡፡ በውጭ ያሉት የዳያስፖራ አባላት ከመንግሥት ጎን የሚንቀሳቀስ ተቋም አድርገው እንደሚገምቱት፣ በአንፃሩ እዚህ ደግሞ ከተቃዋሚ ወገን የሚፈርጁት እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ ይህ ግን የተሳሳተ አመለካከት መሆኑንና ተቋሙ አገራቸውን በሚወዱና ለአገራቸው መሥራት በሚፈልጉ አባላት የሚንቀሳቀስ፣ ዋና ዓላማውም ቢዝነስና ኢንቨስትመንት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲስፋፉ መሥራት እንደሆነ አቶ ዮሐንስ አስረድተዋል፡፡

የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በውጭ ኃዋላ ገቢ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ አስተዋጽኦ እንደሚያበርክት፣ እንዲሁም በአገር ቤት ኢንቨስት ያደረጉ ባለሀብቶች ያስመዘገቡት ካፒታልም በተመሳሳይ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚገመት የዓለም ባንክን ዋቢ አድርገዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ግዙፍ አስተዋጽኦዎችን በማድረግ ላይ የሚገኘው የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በመንግሥት በኩል ሊሻሻሉለት የሚገቡ በርካታ ማነቆዎች እንዳሉም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...