Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የአዳራሽ ሩጫን ገንዘቧ ያደረገችው ገንዘቤ ዲባባ

ትኩስ ፅሁፎች

ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሩጫ በአራት ወርቅና በአንድ የብር ሜዳሊያ ከዓለም ሁለተኛነትን ያገኘችውን ኢትዮጵያን በዋናነት ያገዘፈችው ገንዘቤ ዲባባ ናት፡፡ ሁለት ወርቆችን በ1500 ሜትርና በ3000 ሜትር በማሸነፍ ርቀቶቹን ገንዘቧ አድርጋለች፡፡ በ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቷ ገንዘቤ በማይል፣ 2000 ሜትር፣ 3000 ሜትርና 5000 ሜትር ድሎቿም የገነነች ናት፡፡ የዘንድሮው የ3000 ሜትር ድሏ ለሦስተኛ ጊዜ የተገኘ ሲሆን ያለማሰለስ ክብሩን አጥልቃለች፡፡ መሠረት ደፋር በተመሳሳይ ርቀት አራት ወርቅ አንድ ብርና አንድ ነሐስ ማግኘቷም ይታወሳል፡፡ ፎቶዎቹ ገንዘቤ በሁለቱ ርቀቶች ኔዘርላንዳዊቷን ሲፋን ሐሰንና እንግሊዛዊቷን ላውራ ሚዩርን አስከትላ በመግባት የበላይነት ያሳየችበትን ሒደት፣ ከዚህም በተጨማሪ ቅድመ ውድድር በፊዚዮቴራፒ የተደረገላት የአካል ማፍታታት፣ ከለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሸኛኘት እስከ አዲስ አበባ አቀባበል ያስቃኛሉ፡፡ በ3000 ሜትር ሦስተኛ፣ በ1500 ሜትር 2ኛ የወጣችው እንግሊዛዊቷ ላውራ ሁለተኛ መውጣቷን ተከትሎ ገንዘቤ ‹‹እንኳን ደስ ያለሽ›› ብላ እጇን የዘረጋችላት ቅጽበትን የሚያሳየው ፎቶም የብዙዎችን ቀልብ ገዝቷል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች