የስምንት ዓመቷ ሶርያዊት ስደተኛ ባና አላቤድ፣ ምነው ዓለሙ ሶርያን ችላ አለን ስትል እምባ እየተናነቃት ለሲኤንኤን የዜና ወኪል የተናገረችው፡፡ ሕፃናትን ጨምሮ በመቶ ሺዎች በተገደሉባት አገሯ ለስድስት ዓመታት የዘለቀው እልቂት መቆም አለበት ስትልም ተማፅናለች፡፡ ‹‹ጦርነቱን እንዲያስቆሙት እፈልጋለሁ፣ ብሎም የአገሬ የሶርያ ልጆች ጨዋታ እንዲጫወቱ፣ ትምህርት ቤት እንዲሄዱና በሰላም እንዲኖሩም እፈልጋለሁ፤›› ያለችውም በሲቃ ነው፡፡