‹‹በአዲስ አበባ ከአንድ እስከ አምስት ኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች 38 ናቸው››
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከዓለም ቱሪዝም ድርጅት ጋር በመተባበር ለባለኮከብ ሆቴሎች የተሰጠውን ደረጃ ለማስታወቅ ከተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተወሰደ፡፡ ለደረጃ ይመጥናሉ ተብለው ከቀረቡ 123 ሆቴሎች ውስጥ ሦስቱ አምስት ኮከብ፣ 11 አራት ኮከብ፣ 13 ሦስት ኮከብ፣ 10 ሁለት ኮከብ፣ እንዲሁም አንድ ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡ 31 ሆቴሎች የአደጋ ጊዜ መውጫን በተመለከተ ሰነድ ባለማቅረብ፣ አምስቱ ከመፀዳጃ ጋር በተያያዘ ተገቢውን ሰነድ ባለማቅረብ፣ 21 ያህሉ ደግሞ ሁለቱንም ሰነዶች ባለማቅረባቸው ደረጃ ማግኘት አልቻሉም፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አቶ አሚን አብዱልቃድር ለጊዜው ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎችን ስም ባይገልጹም፣ በቅርቡ ግን ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ቅሬታ ያላቸው ተሰምተው ሥራዎች መጠናቀቅ ስላለባቸው ነው ብለዋል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት ሚኒስትሩ ናቸው፡፡