Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ8400 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የእንቁጣጣሽ ስጦታ ሊያስገኝ ነው

8400 አጭር የጽሑፍ መልዕክት የእንቁጣጣሽ ስጦታ ሊያስገኝ ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (ኢ.ሴ.ማ.ቅ.) የ8400 አጭር የጽሑፍ ሎተሪ ጊዜን እስከ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በማራዘም ለአዲሱ ዓመት የተለያዩ የእንቁጣጣሽ ስጦታዎችን ለመሸለም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ኅብረተሰቡ በአንድ በኩል የሽልማቶች ተጠቃሚ በመሆን በሌላ በኩል ደግሞ ማኅበሩን በማገዝ፣ ማኅበሩ ለሴቶች መብቶች መከበር የሚያደርገውን ጥረት እንዲያሳካና  ሴቶችና ሕፃናት የልማቱ ሙሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል አስተዋጽኦ በማድረግ እንዲሳተፍ ማኅበሩ ጠይቋል፡፡

ከአጭር የጽሑፍ መልዕክት (ኤስኤምኤስ) ሎተሪው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ማኅበር ለጀመረው ማዕከል ማሠሪያ የሚውል ሲሆን፣ ማዕከሉ በውስጡ ለተለያዩ ስብሰባዎችና ሥልጠናዎች የሚውሉ አዳራሾች፣ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎች የያዘ ነው፡፡ ማዕከሉ ከሚሰጠው አገልግሎት  የሚገኘው ገቢም፣ ለጥቃት ሰለባዎችና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ሴቶች ድጋፍ አገልግሎትና ለተያያዥ ሥራዎች የሚውል ይሆናል፡፡

ኢ.ሴ.ማ.ቅ የሎተሪውን አካሄድ ለየት በማድረግ በአንድ ጊዜ ሁለት መልዕክት ለላኩ አንድ ነፃ የሎተሪ ቁጥር በመላክ፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን (አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛን) በመጠቀም መልዕክቱን ለኅብረተሰቡ ሲያስተላልፍ የቆየ ሲሆን፣ ወደፊትም ብዙ መልዕክት ለላኩ ተሳታፊዎች ሰርተፍኬት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት በኢትዮጵያ የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥ የተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ ዓላማውን ለማሳካት የአባል ማኅበራቱን አቅም በማሳደግ፣ ኅብረተሰቡን በማወያየትና ግንዛቤ መስጫ ሥራዎችን በማከናወን፣ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ በመሥራት፣ ምርምሮችን በማድረግ በመረጃ ላይ የተመሠረተ የግፊት (የአድቮኬሲ) ሥራ በመሥራት እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ የተለያዩ አካላት ጋር አጋርነትን በመፍጠር የሴቶች መብቶች እንዲጠበቁ ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ኢ.ሴ.ማ.ቅ ኢትዮጵያዊ ማኅበር ሆኖ በመመዝገቡ ስራዎቹን በዋናነት ከአገር ውስጥ በሚያገኘው ገቢ ያካሂዳል፡፡ በዚሁ መሠረት ዋና የገንዘብ ምንጩ በአገር ውስጥ የሚገኙ ዜጐች የሚለግሷቸው መዋጮዎች ናቸው፡፡ ማኅበሩ በቀጣይ በዘላቂነት የገንዘብ አቅሙን ለማሳደግና ብሎም ስራውን ለማሳለጥ እንዲያመቸው የኢትዮጵያ ሴቶች ማዕከል ሕንፃን ለመሥራት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ገቢ ለማሰባሰብ በ8400 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ከግንቦት 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ኅብረተሰቡን እያሳተፈ ነው፡፡

 እስከ ጳጉሜን 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በሚቆየው አጭር የጽሑፍ መልዕክት ተሳታፊዎችን በተለያዩ የእንቁጣጣሽ ስጦታዎች ለማስደሰት መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም ለ8400 ዕድለኞች የሳምሰንግ ሞባይሎች፣ ቶሺባ ላፕቶፖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ሞተር ሳይከሎች፣ ፍሪጅና እንዲሁም አንድ መኪና መሸለሙ ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...