Saturday, October 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየፀጥታ አስከባሪዎች መጎዳታቸውንና የመሣሪያ መንጠቅ ድርጊቶች መታየታቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ

  የፀጥታ አስከባሪዎች መጎዳታቸውንና የመሣሪያ መንጠቅ ድርጊቶች መታየታቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ

  ቀን:

  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ ጊዜ ጀምሮ 17 የፀጥታ አስከባሪዎች መቁሰላቸውንና የተለያዩ ንብረቶች መውደማቸው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሴክሬታርያት ኃላፊና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. አዋጁ ከታወጀ በኋላ የተከናወኑ ተግባራትን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

  አቶ ሲራጅ አክለውም በተለያዩ አካባቢዎች የመሣሪያ ንጥቂያና የቀበሌ ጽሕፈት ቤቶችን ማቃጠል መፈጸሙን አስታውቀዋል፡፡ አንድ ፋብሪካ መቃጠሉንና አሥር የሕዝብ አውቶቡሶች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

  በተለያዩ አካባቢዎች የታዩ የመንገድ መዝጋት ድርጊቶች እንደነበሩ፣ ነገር ግን አሁን ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑ መስመሮች ክፍት ሆነው አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡ ይሁንና እስካሁን ከአዲስ አበባ ነቀምትና አሶሳ የሚወስዱ መንገዶች ዝግ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ የታሰሩም ሰዎች እንዳሉ አቶ ሲራጅ ጠቁመው፣ ምን ያህል እንደሆኑ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

  በተለያዩ ሥፍራዎች መንግሥት ተዳክሟል እየተባለ እንደሚነገር፣ ሆኖም ይህ የተሳሳተ አመለካከት እንደሆነና አሁን ከየትኛውም ጊዜ በላይ ጠንካራ እንደሆነ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img