ከመላ ኢትዮጵያ የተወጣጡ ትምህርት ቤቶች ተካፋይ የሚሆኑበትና ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ የታዳጊ ወጣቶች የኮፓ ኮካ ኮላ የእግር ኳስ ውድድር አበበ ቢቂላ ስታዲየም መከናወኑን በአዳማ ቀጥሏል፡፡
ኮፓ ኮካ ኮላና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሳምንታት በፊት ለሁለት ዓመታት የሚቆይ የ3.8 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ከሁለቱም ጾታ የተመረጡ 44 ምርጥ ተጨዋቾች በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ለማቀፍ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው ውድድር በሴቶች ምድብ በኦሮሚያ ክልልና በደቡብ ክልል በተካሄደ ግጥሚያ ጀምረዋል፡፡
ይህ ብሔራዊ ውድድር እየተካሄደ የሚገኘው በሁለቱም ጾታዎች ዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች በተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮች የተመረጡ ምርጥ ተጨዋቾች ክልሎቻቸውንና ከተሞቻቸውን ወክለው ነው፡፡
የዘንድሮ የኮፓ ኮካ ኮላ ብሔራዊ ውድድር ነሐሰ 16 ሲጀመር በሴቶች ምድብ ኦሮሚያ ከደቡብ፣ ሐረሪ ከቤኒሻንጉል፣ ኢትዮጵያ ሶማሌያ ከአዲስ አበባ፣ አማራ ከአፋርና ድሬዳዋ ከጋምቤላ ባካሄዱት ማጣሪያ ነው፡፡
ውድድሩ በጥሎ ማለፍና በግማሽ ፍጻሜ ግጥሚያዎች ከተካሄ በኋላ የዋንጫ ግጥሚያ ነሐሴ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ይካሄዳል፡፡
በመክፈቻው ቀን በተደረገ የሴቶች እግር ኳስ ጨዋታ ኦሮሚያ ከደቡብ ክልል 1 ለ1 ሲለያይ፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ በአዲስ አበባ 1 ለ3፣ ጋምቤላ ቢኒሻንጉል 2 ለ6፣ አፋር በሐረሬ 2 ለ3 እና አማራ ከድሬዳዋ 1 ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
የኮፓ ኮካ ኮካ ብሔራዊ እግር ኳስ ውድድር በኮካ ካምፓኒና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትብብር የሚካሄድ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣት ተጫዋቾች ጎልተው የሚወጡበት ዓመታዊ ውድድር ለማድረግ ታቅዷል፡፡