ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ከጳጉሜን 1 እስከ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ሕሙማን ነፃ የምርመራ አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል፡፡
ማዕከሉ ምርመራውን ሊሰጥ ያሰበው ከመንግሥት ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር ሲሆን፣ ለሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት የሐኪም ትዕዛዝ ለተጻፈላቸውና አገልግሎቱ የሚጠይቀውን ገንዘብ ለመክፈል አቅም ለሌላቸው ነው፡፡
ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ከፍተኛ ራዲዮሎጂካል የሕክምና ምርመራ አገልግሎት በመስጠት ግንባር ቀደም የሆነ ተቋም ነው፡፡ ማዕከሉ በተለይም የሲቲ ስካን፣ የኤም አር አይ፣ የአልትራሳውንድ እንዲሁም የዲጂታል ኤክስሬይ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡