ግንባረ ቀይ ጋርዳሚት (Red-Fronted Barbet – Tricholaema diademata) ከላይ ጠቆር ያለ ቡናማ መልክ ያላቸው ወፎች ናቸው፡፡ የታች አካላቸው ብጫ መሳይ ነጭ ሆኖ፣ ከግንባራቸው ላይ ደማቅ ቀይ ምልክት አላቸው፡፡ መንቆራቸው አጭርና ፈርጠም ያለ ነው፡፡ በደረቅ ዛፋምና ከወንዝ አካባቢ በሚገኙ ጫካማ ሥፍራዎች ይገኛሉ፡፡
************
ጥቁርና ነጭ ጡልጥሌ
ጥቁርና ነጭ ጡልጥሌ (Pied Wagtail – Motacilla aguimp) ጥቁርና ነጭ ቀለም ያላቸው ተለቅ ያሉ ወፎች ናቸው፡፡ ከላይ ጥቁር ሆነው፣ ከዓይናቸው በላይ፣ ከአንገታቸው ጎን፣ ከጭራቸውና ከታች አካላቸው ነጭ ናቸው፡፡ በደረታቸው ላይ ጥቁር ጥብጣብ አላቸው፡፡ ባብዛኛው በኢትዮጵያ አካባቢ ይገኛሉ፡፡ የሰው መኖሪያ ዙሪያ ይታያሉ፡፡
- ከበደ ታደሰ ‹‹የኢትዮጵያ መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ወፎች የኪስ መጽሐፍ›› (2000)