Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊመንግሥት የውጪ ዕርዳታ ባይኖርም የተጎዱ ዜጎችን መታደግ የምችልበት አቋም ላይ እገኛለሁ አለ

መንግሥት የውጪ ዕርዳታ ባይኖርም የተጎዱ ዜጎችን መታደግ የምችልበት አቋም ላይ እገኛለሁ አለ

ቀን:

ከውጭ ሰብዓዊ ዕርዳታ ተገኘም አልተገኘም በዝናብ ዕጥረት ለተጎዱ 4.5 ሚሊዮን ዜጎች፣ መንግሥት ዕርዳታ የሚሰጥበት አቅም እንዳለው አስታወቀ፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በበልግና በክረምት ወራት የዝናብ እጥረት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው 4.5 ሚሊዮን ዜጎች ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል 230 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡ መንግሥት ከፍተኛ በጀት በመመደብ ሰብዓዊ ዕርዳታ እየሰጠና የተለያዩ የማካካሽ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አቶ ምትኩ ገልጸው፣ ነገር ግን ዕርዳታ ሰጪዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ሰጡም አልሰጡም መንግሥት በራሱ አቅም ችግሩን ይቋቋማል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጀቶች ነሐሴ 18 ቀን 2007 ዓ.ም. በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ ቀደም ሲል ችግር ውስጥ ከገቡ 2.9 ሚሊዮን ወገኖች በተጨማሪ 1.9 ሚሊዮን ወገኖች ለችግር ተዳርገዋል፡፡

ለእነዚህ ወገኖችም 230 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡ ቀደም ሲል ለችግር ለተጋለጡት 2.9 ሚሊዮን ወገኖች ከሚያስፈልገው በጀት መንግሥት 49 በመቶ ሲሸፍን፣ ቀሪው 51 በመቶ በለጋሾች መሸፈኑን አቶ ምትኩ አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በጥቅሉ ከሚያስፈልገው በጀት አብዛኛው ድርሻ በመንግሥት ይሸፈናል ተብሎ እንደሚጠበቅና የተወሰነው ድርሻ በዕርዳታ ሰጪዎች ሊሸፈን እንደሚችልም አቶ ምትኩ ገልጸዋል፡፡

‹‹ቁም ነገሩ የሚፈለገው ገንዘብ ከዕርዳታ ሰጪዎች የማግኘትና ያለማግኘት ሳይሆን፣ በጀቱ በአጠቃላይ በአገር ውስጥ አቅም ሊሸፈን የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱ ነው፤›› በማለት መንግሥት የተፈጠረውን ችግር አደጋ መቆጣጠር እንደሚችል  አስገንዝበዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብዓዊ ድርጅቶች ከመንግሥት ጋር ሆነው የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች እንዳሉ፣ በእነዚህ ቦታዎች የሚያስፈልገውን ወጪ ለማሰባሰብ የታቀደ ነው በማለት በጋራ የወጣውን መግለጫ ዓላማ አቶ ምትኩ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በበልግና በክረምት ወራት በተስተጓጎለው ዝናብ ምክንያት በበርካታ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ላይ የምግብ ዋስትና ችግር ተጋርጧል፡፡

መንግሥት ይህን ችግር ለመቅረፍ አስቸኳይ ዕቅዶችን ያወጣ ሲሆን፣ የመጀመርያው ዘግይቶ በመጣል ላይ ያለውን ዝናብ ማቀብ፣ ሁለተኛው በአፋጣኝ ለሚደርሱ ሰብሎች ዘር ማቅረብ፣ ሦስተኛ ለአርብቶ አደር አካባቢዎች የእንስሳት መኖ ማቅረብ፣ አራተኛውና የመጨረሻው የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ማቅረብ ናቸው፡፡

በዚህ መሠረት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የአደጋ መከላከልና ዝግጅት ኮሚቴ 700 ሚሊዮን ብር እንዲመደብ በማድረግ፣ የተለያዩ ተግባራት እንዲከናወኑ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ በጀት ውጪም 222 ሺሕ ቶን ስንዴ ግዥ ለመፈጸም ውስን ጨረታ በማውጣት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከአቅራቢዎች ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ይህ ግዥ በዋነኝነት የሚውለው ቀደም ብሎ ከብሔራዊ መጠባቂያ እህል ክምችት ወጥቶ ለተጎጂዎች የተከፋፈለውን ስንዴ የሚተካ ነው፡፡ ከብሔራዊ መጠባቂያ እህል ክምችት 20 ሺሕ ሜትሪክ ቶን እህልና 500 ሜትሪክ ቶን አልሚ ምግቦች እስካሁን በማከፋፈልና እየተከፋፈለም እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዝናብ በተስተጓጎለባቸው አካባቢዎች ዝናብ እየጣለ የሚገኝ በመሆኑ፣ ችግሩን መቆጣጠር የሚቻልበት አመቺ ሁኔታ መኖሩን አቶ ምትኩ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...