Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበይፋ ሥራ የጀመረው አጣሪ ቦርድ በኮማንድ ፖስቱ ማዕከል ላይ ብቻ እንደማይወሰን ገለጸ

በይፋ ሥራ የጀመረው አጣሪ ቦርድ በኮማንድ ፖስቱ ማዕከል ላይ ብቻ እንደማይወሰን ገለጸ

ቀን:

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ሥራውን በይፋ ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲጀምር፣ በኮማንድ ፖስት ማዕከል እንደማይወሰን አስታወቀ፡፡

የቦርዱን ሥራ መጀመር አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የቦርዱ አባላት፣ ባለፈው ዓመት ከነበረው ልምድ በመውሰድ በአሁኑ አዋጅ የምርመራ ሥራው በኮማንድ ፖስቱ ማዘዣዎች ብቻ እንደማይወሰን ገልጸዋል፡፡

የመብት ጥሰቶች ሊከሰቱ በሚችሉበት ቦታ ሁሉ ቦርዱ ተደራሽ እንደሚሆንና ከሕግ ባለሙያዎች ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ በቀለ ሆርዶፋ እንደገለጹት፣ መርማሪ ቦርዱ የሚደርሰውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ ችግሩ የተፈጠረበት ቦታ ድረስ በመሄድ ምርመራ ያደርጋል፡፡ ለዚህም ከኅብረተሰቡ ጥቆማ በተጨማሪ ክትትልና ቁጥጥር የሚያደርግባቸውን ተጨማሪ ሥልቶች መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

የክትትልና ቁጥጥር ሥራው አዋጁ በፓርላማው ከመፅደቁ በፊት ያሉትን 15 ቀናት እንደሚያካትት የጠቆሙት የቦርዱ ሰብሳቢ፣ ‹‹ባለፈው ዓመት የነበረብንን የተደራሽነት ችግር ለመፍታት የሚያስችል አደረጃጀት የፈጠርን ቢሆንም፣ በይበልጥ ከኅብረተሰቡ ጋር ተቀራርበን እንሠራለን፤›› ብለዋል፡፡ 

ኅብረተሰቡ በማንኛውም አካባቢ ኢሰብዓዊ ድርጊት ከተፈጸመ፣ ከቦርዱ በተጨማሪ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጥታ ሊያቀርብ ይችላልም ተብሏል፡፡

ማናቸውንም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕርምጃ በመብት ጥሰት ፈጽሞ ሲገኝ መርማሪ ቦርዱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤትና ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ዕርምጃውን እንዲያስተካክል ሐሳብ እንደሚሰጥም ተነግሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት ብዙ ሰዎች ይታሰራሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው የገለጹት ሰብሳቢው፣ ቦርዱ በኮማንድ ፖስት ማዘዣ አካባቢዎች ሳይወሰን እስከ ወረዳ ድረስ በመዝለቅ ክትትል እንደሚያካሄድም አብራርተዋል፡፡

ኅብረተሰቡም የመብት ጥሰት በሚያስተውልበት ወቅት በስልክ መስመር 011- 154 51 89 ደውሎ ማሳወቅ የሚችል ሲሆን፣ በፋክስ ቁጥር 011 – 154 39 95 በጽሑፍ ሊያቀርብ ይችላልም ብለዋል፡፡

ሰብሳቢውን ጨምሮ የመርማሪ ቡድኑ አባላት ከሁለቱ በስተቀር፣ ዓምና ለ10 ወራት በዘለቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ያገለገሉ ናቸው፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...