Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኮማንድ ፖስቱ ሕገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል አሠራር ዘረጋ

ኮማንድ ፖስቱ ሕገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል አሠራር ዘረጋ

ቀን:

በአገሪቱ በተፈጠረው አለመረጋጋት የመሬት ወረራ ሊካሄድ ይችላል በሚል ሥጋት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያስፈጽም የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በዚህ ተግባር የሚሠማሩ አካላትን በቀጥታ ተጠያቂ የሚያደርግ አሠራር መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ቀደም ሲል ታውጆ በነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያልነበሩ ሦስት ጉዳዮችን አካቷል፡፡ እነሱም በሁከትና ግርግር የሚሳተፉ አካላትን በቀጥታ ተጠያቂ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱና ከጀርባ ሆነው የሚመሩ አካላትም የሚጠየቁበት ልዩ አሠራር አንደኛው ነው፡፡ ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት የሚፈጽሙ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ለምሳሌ በስታዲዮሞች የሚደረጉ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን መነሻ በማድረግ ብሔር ተኮር ወይም ዘር ተኮር ግጭት የሚፈጥሩ አካላትን በቀጥታ ተጠያቂ የሚሆኑበት ልዩ አሠራር ሁለተኛው ነው፡፡ እንዲሁም ሕገወጥ የመሬት ወረራና ሕገወጥ ግንባታ የሚያካሂዱ አካላትን በቀጥታ ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋቱ ደግሞ ሦስተኛው ነው፡፡

የመሬት ወረራና ሕገወጥ ግንባታ ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ችግር እንደሆነ ቢታወቅም፣ አሁን ግን ከሌሎች ጊዜያቶች የተለየ ሪፖርት እስካሁን እንዳልቀረበ ከከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ይጠቁማል፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ዴኤታ ሆነው በቅርቡ የተሾሙት የቀድሞዋ የኦሮሚያ ክልል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ወ/ሮ ሒሩት በራ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአገሪቱ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር የተያያዘ አዲስ የመሬት ወረራና ሕገወጥ ግንባታ ስለመኖሩ ለመሥሪያ ቤታቸው ሪፖርት አልቀረበም፡፡

‹‹በቅርቡ ለቁጥጥር ሥራ ኦሮሚያ ክልል ሄደን ነበር፣ የታየ አዲስ ክስተት የለም፡፡ በካቢኔ ደረጃ በነበረን ውይይትም ይህ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ አልቀረበም፤›› በማለት ወ/ሮ ሒሩት ተናግረው፣ ‹‹ነገር ግን አሁንም ቢሆን ሕገወጥ ግንባታ የአገሪቱ ራስ ምታት ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን አመቺ ጊዜ ነው ተብሎ በሚታሰብበት ወቅት፣ በተለይም በአገሪቱ አለመረጋጋት ሲያጋጥም የመሬት ወረራና ሕገወጥ ግንባታ በሰፊው እንደሚካሄድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ለአብነትም ግንቦት 1997 ዓ.ም. ከተካሄደው ምርጫ በኋላ በገዥው ፓርቲና በቀድሞው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት፣ አገሪቱ አለመረጋጋት ውስጥ ገብታ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዚህ ጊዜ በርካታ የመስፋፊያ ቦታዎች የተወረሩ ሲሆን፣ በዚያ ጊዜ የተፈጠረውን ሕገወጥ ክስተት ዛሬም ድረስ ሙሉ ለሙሉ መፍታት አለመቻሉ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ለአብነት በአዲስ አበባ ከ1988 ዓ.ም. እስከ 1997 ዓ.ም. የተገነቡ ሕገወጥ ግንባታዎችን ሕጋዊ ተደርገዋል፡፡ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ከዓመት በፊት ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ዋዜማና በተለይ ከ1996 ዓ.ም. እስከ 1998 ዓ.ም. ድረስ 5,700 አባላት ያሏቸው ማኅበራት ሕገወጥ ግንባታ አካሂደዋል ብለዋል፡፡

እነዚህን ሕገወጥ ተግባር የፈጸሙትን አካላት አስተዳደሩ ሕጋዊ ያደረጋቸው ሲሆን፣ ሕጋዊ ልናደርግ ይገባል ያሉ አካላትም የአስተዳደሩን ውሳኔ አድሏዊ ነው ሲሉ ቆይተዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን የሚያስፈጽመው ኮማንድ ፖስት በተለያዩ አካባቢዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብለው እንደ ሥጋት የሚታዩት የመሬት ወረራና ሕገወጥ ግንባታዎች ለመከላከል፣ ተጠያቂ የሚሆኑ አካላትን ደግሞ ለሕግ ለማቅረብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውስጥ ተግባራዊ ሊያደርግ ተዘጋጅቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...